በየጭላ አበርገለ ወረዳ ከ483 ሚሊየን ብር በላይ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጀመረ

በየጭላ አበርገለ ወረዳ ከ483 ሚሊየን ብር በላይ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጀመረ አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክ ልል በየጭላ አበርገለ ወረዳ ከ483 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጪ የሚገነባ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተጀመረ። የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ግንባታ ማስጀመሪያ ሥነ ስርዓት ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ተገኝተዋል። ፕሮጀክቱ በሀገር ደረጃ በድርቅ በሚጠቁ ወረዳዎች እየተተገበሩ የሚገኙ የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ፕሮጀክቶች አካል ሲሆን፤ ግንባታው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ትብብር የሚከናወን ነው። በፕሮጀክቱ 4 የውሃ ጉድጓዶች ባለ 100 ሜትር ኪዩብ ሪዘርቬር፣ 2 ባለ 200 ሜትር ኪዩብ የውሃ ማጠራቀሚያ ግንባታ፣ 48 ኪሎ ሜትር የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ 45 የውሃ ቦኖዎች፣ 7 ትምህርት ቤቶችን እና 3 ጤና ጣቢያዎችን ታሳቢ በማድረግ 8 የእንስሳት ውሃ መጠጫ ገንዳዎችንም ያካተተ ነው። ፕሮጀክቱ አንድ ዓመት ከሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ከ30 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

Share this Post