አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ 1000 የመቅዶኒያ ቤተሰቦች ማዕድ ማጋራት ተደረገ።

አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ 1000 የመቅዶኒያ ቤተሰቦች ማዕድ ማጋራት ተደረገ። መስከረም 1/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ1000 የመቅዶኒያ አረጋዊያንና አዕምሮ ሕሙማን መረጃ ማዕከል ቤተሰብ የማዕድ ማጋራት አደረገ። በማእድ ማጋራት መርሃ ግብሩ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች የ2018ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓልን በመቄዶኔያ ከአረጋውያኑ እና አዕምሮ ህሙማን ጋር በማሳለፋቸው በእጅጉ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ክቡር ሚኒስትሩ ወንድማችን ዶ/ር ቢኒያም በለጠ ጧሪ ቀባሪ የሌላቸውን አረጋዊያንና የአእምሮ ህሙማንን ከወደቁበት በማንሳት ሰው ለሰው እንደሚስፈልግና እኛም መተን በዓልን ከነሱ ጋር እንድናሳልፍ ምክኒያት ስለሆንከን በእጅጉ እናመሰግናለን ፤ ፈጣሪም እንደ ቢኒያም አይነቶችን እንዲያበዛልን እንፅልያለን ብለዋል፡፡ አክለውም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ለሜቄዶኔያ የሚደረገውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ስም ቃል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመጨረሻም ሰውን ለመርዳት ሰው መሆኑን በቂ ነው በማለት መልዕክታቸውን አጠቃለዋል ፡፡ ክቡር ዶ/ር ቢኒያምበለጠ እና ታዳሚዎቹ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ላደረገው ማዕድ ማጋራት ወደፊት ለሚደረግላቸው ድጋፍ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ፤ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ክቡር ሚኒስቴር ልዩ አማካሪ መካከለኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

Share this Post