ሁለተኛ የከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እስካሁን በተሰሩ ስራዎች በመጡ ውጤቶችና በቀጣይ ምዕራፍ ስራ የግምገማ ወርክሾፕ ተካሄደ።
ግንቦት 11/2018 ዓ.ም ውኢሚ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሁለተኛ የከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት እስካሁን በተሰሩ ስራዎች በመጡ ውጤቶችና በቀጣይ ምዕራፍ ስራ የግምገማ ወርክሾፕ አካሂዷል።
የወርክሾፑን መድረክ ቁልፍ ጉዳዮችን በማንሳት ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት ዋና ስራ አሰሰፈጻሚ አቶ ኑረዲን መሀመድ ወርክሾፑ በዘርፉ እስካሁን የተሰሩ ስራዎችን ለመገምገምና ቀሪ ስራዎችን በተያዘላቸው ጊዜና በጀት ለማጠናቀቅ ወሳኝ መድረክ ነው ብለዋል።
ዘመናዊ የከተማ ፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ/Fecal Sladge treatment plant /ጨምሮ ሁሉም የሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች ግንባተቸው የደረሰበት ደረጃ፣ ያገጠሙ ችግሮች ፣የታዩ የአሰራር ክፍተቶች የሚለዩበትና የመፍትሔ ሀሳቦች የሚቀርቡበት ወርክሾፕ ነው ብለዋል።
የፕሮጀክቱን ግንባታ የሚከታተሉና የሚያማክሩ ሁሉም የሚመለከተው አካል ለፕሮጀክቱ ግንባታ ስራ ጥራትና ፍጥነት ወሳኝ ሚና ስላላቸው ትክክለኛ መረጃ በመያዝ ፕሮጀክቱ በፍጥነት ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ የሚያስችል ጠንካራ የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።
ግምገማውን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ በመሆን ያደረገ ሲሆን ለግንባታ በተሰጠ በቀሪ 13 ወራት ኮንትራክተሮች በሙሉ አቅማቸው ወደግንባታ በመግባት አጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቃ መደረግ እንዳለበትም ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ከተጠናቀቀ በኋላም ዘላቂና ቀጣይነት ያለውን አገልግሎት እንዲሰጥ ኦፕሬተሮችንና አስፈላጊ የሰው ሀይል በማሰልጠን የተለያዩ ዝግጅቶች መደረግ ስላለበት ሁሉም ተሳታፊ የጋራ ግንዛቤ ይዞ መሄድ አለበትም ብለዋል አቶ ኑረዲን።
በወርክሾፑ የተለያዩ የዘርፉ ሙያተኞች ሰነዶችን አቅርበው ተሳታፊዎች የቡድንና የጋራ ውይይቶች አድርገው በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች አንስተው ከመድረክ ምላሽ፣ ማብራሪያና የወደፊት አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በመድረኩ የሁሉም ክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊዎች፣ ፕሮጀክቶቹ የሚገነቡባቸው የከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊዎ፣ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች፣ የዘርፉ አማካሪዎችና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።