የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች በሕ/ተ/ም/ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር የተለያዩ ፕሮጀክቶች ጉብኝትን ጎበኙ። ጥር 06 /2015 ዓ/ም (ዉ.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች በሕ/ተ/ም/ቤት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢ እና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በሞጆ ከተማ የሚገኙ የባዮ ጋዝ ፕሮጀክቶች ንና የአዳማ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ላይ ጉብኝት አካሄዱ። በሞጆ በቤተሰብ ደረጃ የባዮጋዝ ማብላያ፣ በተቋም ደረጃ የባዮጋዝ ፕሮጀክት፤ እንዲሁም የአዳማ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ የዉሃ ምንጭ የተጎበኘ ሲሆን፤ በቀጣይ የአዳማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አጠቃላይ እንቅስቃሴ፣ የአዳማ ከተማ የሳኒቴሽን መሠረተ ልማቶች እና በአዳማ የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ጽ/ቤት የሥራ እንቅስቃሴዎችን ጎበኙ ።

Share this Post