በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን የነቀምቴ አካባቢ የልማት ስራዎችን ገበኙ።

በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን የነቀምቴ አካባቢ የልማት ስራዎችን ገበኙ።   ነቀምቴ : ጥር 13/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን በነቀምቴ አካባቢ እየተገነባ ያለውን ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት ፣ 274 ሺ የከተማውንና አካባቢውን ማህበረሰብ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እያደረገ ያለውን የጫንጮ ግድብ እና የውሃ ትሪትመንት ማእከል እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ተመልክተዋል።   የነቀምቴ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ፕሮጀክት በሀገር ደረጃ በ22 ከተሞች እየተተገበረ ያለው ፕሮጀክት አካል ሲሆን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ብቁ እንደሚሆንና እስካሁን 80 ከመቶ የግንባታ ስራው የተጠናቀቀ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ፕሮጀክቱ ከተማዋን ውብ ፣ጽዱና ለንሮ አመች እንድትሆን ብሎም የህብረተሰቡን ጤና በመጠበቅና የከርሰምድር የውሃ ሀብት በተለያዩ ቆሻሻዎች እንዳይበከል በማድረግ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ ነው።   74 ሺ የነቀምቴና አካባቢውን ህዝብ ንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርገው ከጫንጮ ግድብ የሚመጣው ውሃ የማንጋኒዝና አይረን ይዘቱ በዘመናዊ መንገድ ትሪት ተደርጎ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም በእለቱ ከተጎበኙ የልማት ሰራዎች አንዱ ነው ። የልማት ስራዎቹን የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር አወቀ ሃምዛ እና አባላቱ ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር አረጋዊ በርሔ እንዲሁም የፌደራል ፣ የክልል እና የዞን አመራሮች በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

Share this Post