ክቡር ሚኒስትሩ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ልኡካን ጋር ተወያዩ፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመሰረተ ልማት ሚኒስቴር ልኡካን ጋር ተወያዩ፡፡ ጥር 4/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የተመራ ሉካን ቡድን ጋር በቢሮአቸው ተወያይተዋል፡፡   ክቡር ሚኒስቴሩ ከልኡካኑ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ለናይል ወንዝ 86% አበርክቶ እያደረገች ቢሆንም የተፋሰሱ ሀገራትን በመደመር መርህ ለጋራ ብልፅግና እና ጥቅም በጋራ መቆም ይጠበቅብናል እያለች ትገኛለች ብለዋል፡፡ ክቡር ሚኒስቴሩ አያይዘውም ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለማንም እገዛ በራስ አቅም የተገነባ በመሆኑ የማንነታችን ምልክት ዳግማዊ አደዋችን ነው ብለዋል፡፡   ኢትዮጲያ ባላት ሀብት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራች ትገኛለች ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ይህንንም ሉካን ቡድኑ ሊገነዘቡት እንደሚገባና ልምዱም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተሞክሮ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል፡፡ እንደ ሌሎቹ የተፋሰሱ ሀገራት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (CFA)ን በመፈረም በትብብር ውሃውን የመጠቀም አስፈላጊነትን በማረጋገጥ ምሳሌ መሆን ይጠበቅባታልም ብለዋል ክቡር ሚኒስትሩ፡፡   ልኡካን ቡድኑም ክቡር ሚኒስትሩ የተናገሩትን ሀሳብ በመደገፍ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለሚመለከተው አካል እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡

Share this Post