የውሃ ሀብት አጠቃቀምንና ፈቀቃድ አሰጣጥን ማዘመን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለፀ።

የውሃ ሀብት አጠቃቀምንና ፈቀቃድ አሰጣጥን ማዘመን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ተገለፀ።   ህዳር 15/2018 ዓ.ም ውኢሚ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከክልል ውሃ ቢሮዎች፣ ከቤዚን አስተዳደር ፅ/ቤቶች፣ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤት እና ከተለያዪ ፕሮጀክቶች ተወክለው ከመጡ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የውሃ ሀብት አጠቃቀምና ፈቃድ አሰጣጥን ማዘመንና /E-Service/አሰጣጥ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል።   የዕለቱን መርሃግብር ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂሚኒስቴር በተቀናጀውሃ ሀብት አሰተዳደር የውሃ አጠቃቀምና ፈቃድ አሰጣጥ ዴስክ ሀላፊ አቶ ጨመዳ ቶሌ የውሃ ሀብት አጠቃቀምንና ፈቃድ አሰጣጥን ማዘመን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል።   አቶ ጨመዳ አክለው ማንኛውም የውሃ ሀብት ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ መሟላት ያለባቸውን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ፍቃድ ማግኘት አለበት ብለው ይህ ዘመናዊ አሰራር የውሃ ሀብትን በፍትሃዊነት፣ በግልፀኝነትና በተጠያቅነት ለመጠቀምና ተደራሽ ለማድረግ ይጠቅማል ብለዋል።   አቶ ሞላ ረዳ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዜርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ በበኩላቸው የወርክሾፑ ወጪ በሙሉ የተሸፈነው በባዜርኔት ፕሮጀክት በጀት መሆኑን ገልፀው የውሃ ሀብት አጠቃቀምን የማዘመንና ፈቃድ አሰጣጥ ሂደቱን ቀላልና ፈጣን ለማድረግ ወርክሾፑ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም አብራርተዋል።   አቶ ሞላ አያይዘውም የፈቃድ አሰጣጡን የማዘመን ሂደቱ አንድ ዓመት የፈጀ እንደሆነና ስራው የባዜኔትር ፕሮጀክት ከተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት የሚተገበር መሆኑን ገልፀዋል። ለተሳታፊዎች አጠቃላይ የውሃ ሀብት አጠቃቀምና ፈቃድ አሰጣጥ ሂደቱ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ሰነድ ያቀረቡት በተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳዳር የውሃ ፈቃድ አሰጣጥ ባለሙያ አቶ አየለ አጥለው ፈቃድ አሰጣጡን ማዘመን ለፈጣን አገልገሎት፣ ወጪ ለመቆጠብና ከወረቀት ነፃ አገልግሎት ለማቅረብ ጠቃሚ እንደሆነ አብራርተዋል።   ፈቃድ አሰጣጡን ማዘመን ያስፈለገበትን ምክንያት አቶ አየለ ሲያብራሩ ከዚህ ቀደም የነበረው ፈቃድ አሰጣጥ ቅንጅታዊ አሰራር የማይታይበት፣ የተበታተነና የተበጣጠሰ በመሆኑ ጊዜ የሚፈጅ፣ ተጠያቂነትና ግልፀኝነት ያልነበረው በመሆኑ ዘመናዊ ፈቃድ አሰጣጥ እነዚህን ክፍተቶች በሙሉ የሚሞላ ነው ብለዋል።   አቶ አየለ ባቀረቡት ሰነድ የውሃ ፈቃድ የሚያስፈልጋቸውና የማያስፈልጋቸው የውሃ ሀብት ዓይነቶች፣ ፈቃድ ጠያቂው ምን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት እንዳለበት፣ ፈቃዱ እንዲሰረዝ የሚያስገድዱ ሁኔታዎችና ፈቃዱን ለማግኘት የሚፈጀው ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ በሰፊው አብራርተዋል።   ዘመናዊ የውሃ ሀብት አጠቃቀምና ፈቃድ አሰጣጡን /E-Srvice/ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በቅንጅት ያዘጋጀው /Develop/ ያደረገው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲሆን በዕለቱ ሚኒስቴሩ ተወክለው የመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ለተሳታፊዎች ስለቴክኖሎጂው ማብራሪያ ሰጥተዋል። በቀረቡት ሰነዶች ላይ ተሳታፊዎች ጥያቄና አስተያየታቸውን አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎ ማብራሪያም ተሰጥቷል፤ በነበረው ቆይታ ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኙም ገልፀዋል ።

Share this Post