በባዘርኔት ፕሮጀክት አተገባበርና ውጤታማነት ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

በባዘርኔት ፕሮጀክት አተገባበርና ውጤታማነት ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።   ጥቅምት 19/2018 ዓ/ም ውኢሚ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአዋሽና በዋቢሸበሌ ተፋሰሶች ላይ የባዜርኔት ፕሮጀክት አተገባበር፣ ውጤታማነትእና የህብረተሰብ ተጠቃሚነት ዙሪያ ለፕሮጀክቱና ለተፋሰሶቹ ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል።   ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ብዙነህ አሰፋ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ብሔራዊ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተባባሪ ስልጠናው በአዋሽና በዋብሸበሌ ተፋሰሶች ላይ በባዜርኔት ፕሮጀክት ለሚተገበሩ ስራዎች ውጤታማነትና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ባለሙያዎቹ እና የሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ እንዲጨብጡ ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።   የባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እና ስለፕሮጀክቱ አተገባበር በቂ ግንዛቤ መጨበጥ ህብረተሰቡ ለፕሮጀክቶች የባለቤትነት ስሜት እንዲኖራቸው እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሚየግዝም ዶ/ር ብዙነህ ገልፀዋል።   ህብረተሰቡ በተለያዩ ፕሮጀክቶች አተገባበር ላይ ተሳታፊና ተጠቃሚ ሲሆን የፕሮጀክቶቹ በውጤታማነት፣ ቀጣይነትና ዘላቂነት ይረጋገጣልም ብለዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዘርኔት ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በአጠቃላይ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር በዓለም ሀገራት የነበረውን ተሞክሮ በማየት በሀገራችን በተሻለና ውጥታማ በሚያደርግ መልኩ ለመተግበር ታስቦ ተዘጋጅቷል ብለዋል።   ለአንድ ፕሮጀት ውጤታማነት ትብብር፣ ቅንጅታዊ አሰራርና የጋራ ግንዛቤ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ሞላ ከከፍተኛ አመራር እስከ ማህበረሰቡ ድረስ ሰለ ፕሮጀክቱ ተመሳሳይ መረዳት እንዲኖር ስልጠናው እጅግ ጠቃሚ ነውም ብለዋል። በስልጠናው የሁለቱ ተፋሰሶችና የፕሮጀክቱ ሀላፊዎችና የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚመለከታቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post