ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ኢነርጂ ወሣኝ መሆኑ ተገለፀ ።
ጥቅምት18/2018 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ)በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተዘጋጀው 2ተኛው የውሀና ኢነርጂ ሳምንት አውደርእይ እና ፓናል ላይ ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ኢነርጂ ወሣኝ መሆኑ ተገለጸ።
ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው አውደርእይና ፓናል ላይ የኢነርጂ ዘርፉን ፓናል ውይይት የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ እንደገለፁት ቀጣይነት ያለው የኢነርጂ አቅርቦት ሀገራችን ለያዘችው ብልፅግና ወሳኝና የጀርባ አጥንት መሆኑን ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በሀገራችን አብዛኛው የህብረተሠባችን ክፍል የባዮ ማስ ተጠቃሚ በመሆኑ የእፅዋቶች መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀነስ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የአፈር መሸርሸር ምክኒያት የግብርና ምርትና ምርታማነት በመቀነስ የምግብ ዋስትና እንዳናረጋግጥ ከማድረጉም በላይ በጭስ ምክኒያት ህብረተሠባችን ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጠ መሆኑን በንግግራቸው ገልፅዋል።
አክለውም ከለውጡ በኃላ የኢነርጂ አቅርቦት እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ከህብረተሰባችን ብዛት፣ የመልከአምድር አቀማመጥና ስርጭት አኳያ በቂ አለመሆኑንም ተናግረዋል።
በመጨረሻም የኢነርጂ አቅርቦቱ የሀገራችንን ፍላጎት አሟልቶ ምስራቅ አፍሪካን አገናኝቶ የሚያልፍ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፓሊሳችንን መከለስና የግል ሴክተሩን ማሳተፍ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።
በእለቱ በታዳሽ ሀይል አቅርቦት፣ ስርጭትና ተደራሽነት ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።