ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ተቋማዊ ራእይን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው ተባለ።

ጥራት ያለው የአገልግሎት አሰጣጥ ተቋማዊ ራእይን እውን ለማድረግ ወሳኝ ነው ተባለ። ታህሳስ 2015 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመሪሮች፣ አማካሪዎች እና የቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊዎች ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዳማ እየተሰጠ ይገኛል። በስልጠናው የተገኙት የውሃና ኢነርጅ ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኦልቀባ ባሸ አንድ ተቋም ያስቀመጠውን ራእይ ለማሳካት ከሚያግዙ ዋና ዋና መስፈርቶች መካከል ጠንካራና ግልጽ የሆኑ እሴቶችን በጥንቃቄ በመቅረጽ እና የተቋሙ ሰራተኞች በጥልቀት እንዲገነዘቧቸው ማድረግ መሆኑን ጠቅሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከቀረጻቸው 9 እሴቶች ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት አንዱ በመሆኑ የደንበኞችንና አጠቃላይ የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማርካት አገልግሎቱን በሚፈለገው ጥራትና ቅልጥፍና ማቅረቡ የማህበረሰቡን ጠንካራ እምነት ከማግኘት ባለፈ ጥሩ የሆነ የመሪና ተመሪ ግንኙነት እንዲኖር ብሎም በጎነት የተሞላበት የስራ ቦታና ባህል እንዲጎለብት ያግዛል ብለዋል። ለውጥን መፈለግ ከሰው ተፈጥሮ ጋር አብሮ የተገመደ ነው ያሉት ዋና ስራ አሰፈጻሚው አልፎአልፎ ከተለያዩ አሉታዊ ተጽእኖዎች የተነሳ ከለውጥ የመሸሽ ዝንባሌ ቢታይም ለውጥን መፈለግ ብቻ ሳይሆን ጥብቅ ትስስርም ስላለው ከመሪው ያልጀመረ ለውጥ ዘላቂነቱ ያን ያክል በመሆኑ የለውጥ ባህሪያትን በሚገባ በመገንዘብ የለውጥ አካል መሆንና መልካም አጋጣሚዎችነ በመጠቀም ለስራና ሰራተኛው ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጣችን በማሻሻልና ተቋማዊ ራእዩን እውን ማድረግ ይገባልም ብለዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ሁሉም በየዘርፉ ስራውን በተገቢው ጊዜና የጥሪት ደረጃ ለማከናወን የለውጥ አስፈላጊነትን ተረድቶ የለውጥ አካል ለመሆን የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር ጉዳይ አማራጭ የሌለው መሆኑን ተረድተን ስልጠናውን በሚገባ ተከታትለን ከስልጠናው የሚጠበቀዉ ውጤት ግብ እንዲመታ የድርሻችንን እንወጣ ሲሉ ዋና ስራ አስፈጻሚው አሳስበዋል። በእለቱ የአገልግሎት ለውጥ መነሻ፣ የመንግስት ተቋማት ዋና ዋና ችግሮች፣ የቀጣይ የሪፎርም አምዶች፣ የለውጥ መንስኤዎች፣ የአግልግሎት ጥራት መለኪያዎች እና የአገልግሎት ጥራት ማእቀፍ የሚሉና ሌሎች ተያያዠ ጉዳዮች በስልጠናው ትኩረት ተደርጎባቸዋል።

Share this Post