ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጡ፡፡
ጥቅምት 18/2018 (ው.ኢ.ሚ) ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው፡፡
6ኛው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከም/ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ምላሽና ማብራሪያ ሰጡ፡፡
በመደበኛ ስብሰባው በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ ተጠሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡