ኢትዮጵያ በውሃና ኢነርጂ ልማት ዘላቂነት ያለውና ለጋራ ብልፅግና መሪ ሚና እየተወጣች መሆኑ ተገለጸ።
ጥቅምት 17/2018(ውኢሚ)፦ ኢትዮጵያ በውሃና ኢነርጂ ልማት ዘላቂነት ያለውና ለጋራ ተጠቃሚነት መሪ ሚና እየተወጣች ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በውሃና ኢነርጂ ሚኒሰቴር የተዘጋጀውን 2ኛውን የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት በሳይንስ ሙዚየም በመከኘት ከፍተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት በውሃ እና ለአረንጓዴ አሻራ ላይ ትኩረት ሰጥታ በመስራቷ ብዙዎችን ተጠቃሚ እያደረገች መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የቀጣናው የኃይል ማዕከል እየሆነች ሲሆን ለሱዳንና፣ ለጂቡቲ እና ለኬንያ ታዳሽ ኃይል እያቀረበች እና አፍሪካ ዘላቂ የውሃና ኢነርጂ ዋስትናዋን እንድታረጋግጥ መሪ ሚናዋን መወጣቷን እንደምትቀጥልም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በተያያዘ በመርሀ ግብሩ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ 2ኛው የውሀና ኢነርጂ ሳምንት ሀገራችን በታዳሽ ኢነርጂ ፣ ኢትዮጵያ የውሃ ሃብት ጥበቃና አጠቃቀምን በተመለከተ ትርጉም ያላቸውን ስራዎች እየሰራች ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የውሃ ሃብት ጥበቃ ላይ የምትሰራው ስራና የኃይል ልማት ተግባራት ለሌሎች ትምህርት የሰጠ መሆኑንም ገልጸዋል።
በ2ተኛው የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት ላይ ዐውደ ርዕይና ፓናል ውይይቶች እንደሚደረጉና በፓናል ውይይቱም ላይ የውሃ ሃብት አጠቃቃም እና አስተዳደር የተመለከተ እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ላይ ያሉ ልምዶችን የተመለከቱ ጉዳዮች እንደሚዳሰሱ ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል።