ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በሚል ርዕስ ስልጠና ተሰጠ።

ብሔራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በሚል ርዕስ ስልጠና እየተሰጠ ነው። ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ እና የመስኖና ቆላማ ሚኒስቴር አመራሮችና ሠራተኞች በሐገራዊ ጥቅምና ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና ላይ አቅምን የሚያጎለብት ስልጠና እየተሰጠ ነው። ስልጠናውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ስልጠናው የሚያተኩርባቸው ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች የኢትዮጵያ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናና ብሔራዊ ጥቅም፣ የብሔራዊ ጥቅም ዋነኛ ፈተናዎች፣ ለብሔራዊ ጥቅም መረጋገጥ ቁልፍ መፍትሔዎች፣ ለብሔራዊ ጥቅሞቻችን መረጋገጥ የሚጠበቅብን ሚና እና የተቋማት ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በተቋም ውጤታማነት ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ በዝርዝር ለአመራሩና ለሠራተኛው ግንዛቤ በሚፈጥር መልኩ አብራርተው በዝርዝር ስልጠናው ስልጠናውን እየሰጡ ነው። ክቡር ሚኒስትሩ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ላይ ውስጣዊ አንድነታችንን በማጠናከር በጋራ መቆም እንዳለብንም አክለዋል። ስልጠናው ላይ የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ባለሙያች የተሳተፉ ሲሆን ለግማሽ ቀን የሚቀጥል ይሆናል።

Share this Post