በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ዶ/ር የተመራው ልዑክ በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ገሬኖ እንሰት ተክል ላይ Children Investement Fund Foundation(CIFF) እያስገነባው ያለውን የንፁህ መጠጥ ውሃን ምልከታ አደረጉ።
ጳጉሜ 05/2017 ዓ.ም (ወልቂጤ)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ገሬኖ እንሰት ተክል የሶላርና የንፁህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ስራ የደረሰበትን የፌዴራል ፣ የክልል ፣ የዞንና የሚመለከታቸው የውጭ ዜጎች በተገኙበት ምልከታ የመስክ ላይ ምልከታ ተደርጓል ።
የፕሮጀክቱ ፕሮግራም እንደ ሀገር በስምንት ክልሎች የሚካሄድ ሲሆን በስምንቱ ክልሎችም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የምልከታው አካል ነው ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ላይ የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆኑት ከሪስቶፎር አንቶኒ ተገኝተው እንደ ሀገር ሲሰሩ የቆዩት ስራዎች ምልከታ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።
የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆኑ ከሪስቶፎር አንቶኒ በምልከታው ወቅት እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ እና የተጓደሉ አሰራሮችን በማረም ጠንካራ አፈፃፀሞች እንዲጎለብቱ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ምልከታ እንደሆነ ተናግረዋል ።
ገሬኖ እንሰት ተክል በመንግስት ጤና ኬላና ትምህርት ቤት ላይ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት መፀዳጃ ቤት እና ቆሻሻ ማቃጠያ የግንባታ ሰራ የተሰራ ሲሆን እንዲሁም የንፁህ መጠጥ ዉሃ ለተቋማት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል።
በምልከታው ወቅትም የኢፌድሪ ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስተር ሚኒስቴር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የክልሉ ዉሃ፣ መስኖና ማዕድን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ አለይካ ሸኩር፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የትምህርት ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስከብር ወልዴ፣ የዞኑ ውሃና ማዕድን ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ መሀመድ አማን፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ የመንግስት አላፊዎች ተገኝተዋል።