በኢነርጂው ዘርፍ ባለፉት ሰባት ዓመታት እመርታዊ ለውጥ መመዝገቡ ተገለጸ።

በኢነርጂው ዘርፍ ባለፉት ሰባት ዓመታት እመርታዊ ለውጥ መመዝገቡ ተገለጸ። በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት አመታት በኢነርጂው ዘርፍ እመርታዊ ለውጦችን ማስመዝገብ መቻሏ ተገለጸ፡፡ ጳጌሜ/2017ዓም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በነበረው በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ በተዘጋጀው ሳይድ ኤቨንት ላይ ባደረጉት ንግግር ሀገራችን ከሀይል አቅርቦትም ሆነ ተደራሽነትን ከማሳደግ አንጻር አመርቂና አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገቧን በመግለጽ ለዚህም ፖሊሲ በማርቀቅም ሆነ በማክሮ ኢኮኖሚው ላይ የተደረጉ ሪፎርሞች አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በዚሁ ጉባኤ በተደረገው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ውይይት ላይም ኢትዮጵያ ከሀይል ዘርፍ ልማት እና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ከማሳግ አንጻር የሰራቻውን መጠነ ሰፊ ስራዎችን አስመልቶ ልምድ ያካፈሉ ሲሆን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ላይ እንዴት የኢነርጂውን ዘርፍ ለማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ለውጡ አስተዋጽኦ እያደረገ እንዳለ ማብራያ አቅርበዋል፡፡ ያልተማከሉ የኢነርጂ መሰረተ ልማቶችንም ምርትና ምርታማነትን ለማሳግ ያላቸውን አስተዋጽኦ አብራርተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ለተከታታይ ሰባት ቀናት ሲካሄድ የነበረውና በተለያዩ የአየር ንብረት ለውጦችና ተያያዥ ጉዳዮች ሲመክር የቆየው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ በዛሬው እለት ይጠናቀቃል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

Share this Post