የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት አሰጣጥ ተቆጣጣሪ አካል ማቋቋሚያ ማዕቀፍ ላይ ውይይት ተደረገ።
የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት አሰጣጥ ተቆጣጣሪ አካል ማቋቋሚያ ማዕቀፍ ላይ ከክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮዎች ሀላፊዎች፣ የከተማ ውሃ አገልግሎት ስራ አስኪያጆችና ባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።
ነሐሴ 14/2016 ዓ/ም (ወ.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀ የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት አሰጣጥ ተቆጣጣሪ አካል ማቋቋሚያ የህግ ማእቀፍ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮዎች ሀላፊዎች፣ የከተማ ውሃ አገልግሎት ስራ አስኪያጆች እና ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሄደ።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የከተማ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ዴስክ ሀላፊ በሆኑት በወ/ሮ አዜብ ታደሰ የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ተቆጣጣሪ አካልና ማቋቋምን በተመለከተ ጽሑፍ አቅርበዋል።
በተጨማሪም ከዛምቢያና
ከብራዚል በመጡ ከፍተኛ የዘርፉ አማካሪዎች አለምአቀፍ ተሞክሮዎች ቀርበዋል።
የደረጃዎች ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር መሠረት በቀለ የከተማ የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት አሰጣጥ ተቆጣጣሪ አካል ማቋቋም ጠቃሚነቱን አንስተው፤ ደረጃ የመስጠት ሂደቱን በተመለከተ ለተፈጻሚነቱና ለውጤታማነቱም ተቋማቸው የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል።