በቤና-ጸማይ ወረዳ የቀይ አፈር ከተማ ከ15 ሺ በላይ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ።

በቤና-ጸማይ ወረዳ የቀይ አፈር ከተማ ከ15 ሺ በላይ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ። ግንቦት 4/2018ዓም (ው.ኢ.ሚ​) በደቡብ ኦሞ ዞን በቤና-ጸማይ ወረዳ የቀይ አፈር ከተማ ከ15 ሺ በላይ ነዋሪዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ የምርቃት መርሀ ግብር ላይ የተገኙት እና የእለቱ የክብር እንግዳ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ መንግስት በክልሉ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በተለይ በመጠጥ ውሃና በጤና ላይ በመስራት ህዝባዊነቱን አሳይቷል ብለዋል። በመጨረሻም አቶ ንጋቱ ህብረተሰቡ ፕሮጀክቱን በቁጠባ ለተፈለገለት አላማ ብቻ በመጠቀም እንዲሁም ተመጣጣኝ የአገልግሎት ክፍያ በመክፈል ውሃ አገልግሎቱን በማሳደግ ሌሎች ልማቶችን መስራት አለበት በማለት አሳስበዋል። በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ በክልሉ እንደ ፌደራል መስሪያ ቤት በኢነርጂ፣ በውሀ ሀብት አስተዳደር እንዲሁም በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ትላልቅ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ መሆኑን ገልጸው የቀይ አፈር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው ብለዋል። ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የክልሉን የመጠጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን ሰርቶ ለከተማዋ ውሃ አገልግሎት ያስረከበ ቢሆንም ማስቀጠል ግን የህብረተሰቡ ኃላፊነት ነው ብለዋል። ​ ክቡር አምባሳደር ፕሮጀክቱ የህዝብ ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ፣ በከተማዋ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ አዲስ ተስፋን ይዞ የሚመጣ እና የእናቶችና ህፃናት ውሃ ፍለጋ የሚንገላቱበትን ጊዜም በዘላቂነት ያስቀራል ብለዋል። ፕሮጀክቱ ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባና ከ15 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለ20 አመት ተጠቃሚ ማድረግ የሚችል መሆኑንም ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ ​በሰከንድ 16.8 ሊትር የሚያመነጭ፣ ​500 ሜትር ኩብ የሚይዝ የውሃ ማጠራቀሚያ፣ ​ከ28 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝም የቧንቧ ዝርጋታእንዲሁም ​6 አዳዲስ የህዝብ የውሃ መጠጫዎችና ዘመናዊ የንፅህና መጠበቂያ (መጸዳጃ) ቤቶች ያካተተ መሆኑም ተገልጿል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢንጅነር አክሊሉ አዳኝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክልላቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነዋል። በእለቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የምርቃቱ አንዱ አካል ሆኖ ተከናውኗል። ​በመርሀ ግብሩ ላይ የፊደራል፣ የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post