ኢትዮጵያ ለCOP32 የምታዘጋጀው አረንጓዴ አሻራ 🌱🌍
ኢትዮጵያ ለCOP32 የምታዘጋጀው አረንጓዴ አሻራ
ኢትዮጵያ ለምታዘጋጀው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32) ዝግጅት ከፕሮጀክቶችና ከመሠረተ ልማቶች ባሻገር፣ የአረንጓዴ ልማት አሻራን ማጠናከር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶታል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ እና የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሱልጣን ወሌ፣ ከአርሴማ ድልድይ እስከ ኮዬ ፈጪ ባለው አካባቢ እየተከናወነ ያለውን የችግኝ ልማትና የአረንጓዴ ልማት ሥራ ዕለት በዕለት በመስክ በመገኘት እየተከታተሉ ይገኛሉ።
የመስክ ክትትሉ የሚያሳየው፣ ለCOP32 ዝግጅት የሚደረገው ሥራ በስብሰባ አዳራሽ ብቻ ሳይሆን በመሬት ላይ በተጨባጭ ውጤት እንዲገለጽ የተያዘውን ቁርጠኝነት ነው።
በየዕለቱ በመስክ በመገኘት የችግኝ ልማቱን ደረጃ መመልከት፣ በተግባር ያሉ ችግሮችን መለየት፣ ለሚመለከታቸው አካላት የሥራ መመሪያ መስጠትና የሚፈለገው ውጤት በጊዜው እንዲረጋገጥ ማድረግ የክትትሉ ዋና አካል ነው።
ዛሬም እንደወትሮው ሚኒስትሩና ሚኒስትር ዴኤታው በመስክ በመገኘት የችግኝ ልማቱን ሁኔታ በመገምገም፣ በሥራ ላይ ያሉ አፈጻጸሞችን በመከታተልና ለሥራ አስፈጻሚዎች የሥራ መመሪያ ሲሰጡ የሚያሳየው ፎቶ የዚህ ተግባራዊ ክትትል ምስላዊ ማሳያ ነው።
አረንጓዴ አሻራ ዛሬ የሚተከል፣ ነገ የሚያጠልል ተስፋ ነው!
COP32 — የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት አሻራ ለዓለም!