ለአዋሽ ተፋሰስ የውሃ መረጃ አንባቢዎች የ3 ቀናት የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጀመረ።
በቤዚን አቀፍ የዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄድ ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ከሚተገብራቸው አምስት ቁልፍ ተግባራት መካከል በተፋሰስ የሚሰበሰቡ የውሃ ሀብት መረጃዎችን በሥርዓት ማስቀመጥ፣ በዘመናዊ መንገድ ማደራጀት እና የተቋማትን እንዲሁም የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበትን የሚመለከተውን ቁልፍ ተግባር ለማሳካ