የባዝርኔት ፕሮጀክት የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ አቀረበ

የባዝርኔት ፕሮጀክት የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ አቀረበ፡፡

በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሥር የሚተገበረው የባዘርኔት (BASRINEt) ፕሮጀክት የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ለብሔራዊ ቴክኒካል ኮሚቴ አቀረበ።

ነሐሴ22/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ፕሮግራሙን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ ውሀ ሃብት አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ደበበ ደፈርሶ መርተውታል።

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ክንውኖች፣ አፈጻጸሞች እና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ አቅርበዋል።

አቶ ሞላ ፕሮጀክቱ በዋናነት አምስት ኮምፖነንቶች እንዳሉት በመግለጽ ባለፈው በጀት አመት በዋናነት የውሃ ሀብት እና መሰረተ ልማት ልማት በሦስት የፕሮጀክት ትግበራ ቦታዎች ላይ የውሃ አማራጮች መለያ እና ካርታ የማዘጋጀት ሥራ ተጠናቋል፣የ16 ኪሎ ሜትር የታችኛው አዋሽ ወንዝ የጎርፍ መከላከል እና የቦይ ማቋቋሚያ ጥናት የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ለ3 አነስተኛ መስኖ እና 4 የውሃ አቅርቦት ስራዎች ጥናት መጀመሩን፣13 የውሃ ጥራት እና ደለል መከታተያ የላቦራቶሪ ዕቃዎች ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ላይ መሆናቸውን፣በአዋሽ እና በዋቢ-ሸበሌ ተፋሰሶች 10 የቴሌሜትሪ ቅድመ-ተከላ ቦታዎች የተረጋገጡ ሲሆን፣ ለ6 የሙከራ እና 5 የመከታተያ የከርሰ-ድርጅት ጉድጓዶች የግዥ ሂደት በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የተፋሰስ እንክብካቤ እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይም የተፋሰስ እና ወሰን ክልል እንክብካቤ ማዕቀፍ እንዲሁም የመሬት አጠቃቀም ምዘና 100%የተጠናቀቀ መሆኑን በመግለጽ የአቅም ግንባታ እና ማህበረሰብ ሰፊ እንቅስቃሴ መደረጉንም በሪፖርታቸው ገልጸዋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ መፍትሄዎች የቀረቡና በኮሚቴዉ ተሳታፊዎች ዉይይት ከተደረገበት በኋላ የ2019 ዓ.ም የፕሮጀክቱ ዓመታዊ የሥራና የበጀት እቅድም በአስተባባሪው ቀርቧል፡፡

በሪፖሪቱ ዋና ዋና ተግባራት እና የአመቱ በጀት በኮምፖነንት ቀርቦ በዚህ መሰረት የበጀት አመቱ አጠቃላይ በጀት በጣም ከፍተኛ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን፤ይህንን ለማሳካት አስፈላጊዉን ስልት በማዉጣት ለማከናወን እንደታለመ እና ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትና ፈጻሚዎች ተገቢ ድጋፍ ከተደረገ ማከናወን አንደሚቻል ተጠቅሷል።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች አቶ ሞላ ረዳ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ደበበ ደፈርሶ በተሳታፊዎች በቀረቡት ጉዳዮች ላይ መሻሻል የሚገባቸዉ ነጥቦች እንዲሻሸሉ አቅጣጫ በመስጠት ስብሰባዉ አጠቃለዋል።

በፕሮግራሙ ከውሃና ኢነርጂ ፣ከግብርና እና ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ AICS እናሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post