የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሞ መድረኩን አጠናቋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሞ መድረኩን አጠናቋል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመገምገም፣ በመጠጥ ውሃ፣ በሳኒቴሽን፣ በኢነርጂ ልማት እና በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችን እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር ገምግሟል።
በግምገማው ወቅት በተቋማዊ ሪፎርም፣ በአገልግሎት ጥራት፣ በሰው ኃይል ልማት፣ በገንዘብ አጠቃቀም፣ በውሃ አገልግሎት ፍትሃዊነት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣ በአሰራር ስርዓት ማዘመን፣ የልምድ ልውውጥ ባህልን ማጠናከር እና የቅሬታ አቀራረብ ስርዓትን ማሻሻል ላይ የተለያዩ የማሻሻያ ሐሳቦች ቀርበው፣ በተነሱት ጉዳዮችም ተገቢ ምላሽ ተሰጥቷል።
በተለይም በንብረት ማስወገድ ሥራ ላይ ሚኒስቴሩ ከሌሎች የፌዴራል ተቋማት በተሻለ አፈጻጸም በማሳየቱ ተሸላሚ መሆኑ በግምገማው ተገልጿል።
በአጠቃላይ በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ሥራዎች በርካታ አበረታች ውጤቶችን እንዳስመዘገቡ የተገለጸ ሲሆን፣ በቀጣይ ወቅት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት የአገልግሎት ጥራትን፣ ተቋማዊ ብቃትን እና የአሰራር ውጤታማነትን የበለጠ ለማሻሻል የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።
በዚሁ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ የቀረቡ አስተያየቶችና የተሰጡ ግብረመልሶች በቀጣዩ የሥራ ዘመን የተሻለ አፈጻጸምና ውጤታማ አገልግሎት ለማረጋገጥ መሠረት እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።