የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት የአፈጻጸም ማንዋል አተገባበር ውይይት ተደረገበት
የቤዚን አቀፍ ዘላቂነት ማረጋገጫ ፕሮጀክት የአፈጻጸም ማንዋል አተገባበር ውይይት ተደረገበት
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) — በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተተገበረ የሚገኘው የባዘርኔት ፕሮጀክት የአፈጻጸም ማንዋል (BaSRINET Project implementation manual) አተገባበርን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።
ውይይቱ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም በተቀናጀ፣ በተደራጀና በውጤታማ መንገድ ለመምራት የተዘጋጀው የአፈጻጸም ማንዋል በተግባር እንዴት ሊተገበር እንደሚችል ለመወያየትና የባለድርሻ አካላትን ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ ነው።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ፣ የአፈጻጸም ማንዋሉ ፕሮጀክቱን በቀጣይ የትግበራ ሂደት በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ለመምራት ጠቃሚ የአፈጻጸም መሣሪያ መሆኑን ገልጸዋል።
ማንዋሉ የፕሮጀክቱን ዓላማዎችና የአፈጻጸም አቅጣጫዎች በግልጽ ለመለየት ከማገዙም በላይ በፕሮጀክቱ የሚሳተፉ አካላት የየራሳቸውን ሚናና ኃላፊነት በተገቢው መንገድ እንዲወጡ የሚያስችል የጋራ የትግበራ ሰነድ መሆኑን ተጠቁሟል።
የልማት አማካሪው ዶክተር አድማሱ ቴሶ የማንዋሉን ዝርዝር ይዘት በማቅረብ፣ ማንዋሉ የፕሮጀክቱን ትግበራ ሊያግዝ በሚችል መልኩ በተለያዩ ይዘቶችና ምዕራፎች መደራጀቱን አብራርተዋል።
በማንዋሉ የዝግጅት ዘዴ፣ ዓላማና ጥቅም፣ ተቋማዊ የአመራር ሥርዓት፣ የዕቅድ አፈጻጸም ይዘቶች፣ የፕሮጀክቱ አስተዳደር ይዘቶች፣ የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ሥርዓት እንዲሁም የትግበራ ስልቶች ተካተዋል።
በውይይቱ ወቅትም ማንዋሉ በትግበራ ሂደት ቀላል፣ ግልጽና ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችሉ ማሻሻያ ሐሳቦችና አስተያየቶች ከተሳታፊዎች ቀርበው ምክረ ሀሳቦች ተሰንዝረዋል።
በመድረኩ የተነሱት ሐሳቦችና አስተያየቶች የፕሮጀክቱን የአፈጻጸም ማንዋል በቀጣይ የትግበራ ሂደት የበለጠ ተግባራዊ፣ ግልጽና ውጤታማ ለማድረግ ጠቃሚ ግብዓት እንደሚሆኑ ተገልጿል።
የአፈጻጸም ማንዋሉ ስትራቴጂካዊ የትግበራ ሰነድ በመሆኑ፣ የፕሮጀክቱን ዓላማዎች ለማሳካት የሥራ ሂደቶችን በግልጽ አቅጣጫ ለመምራት፣ ተግባራትን በቅንጅት ለማከናወንና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማጠናከር ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ተመልክቷል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto