ስፔሻላይዝድ ላብራቶሪው የአገሪቱን የውሃ ሃብት ጥራትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ
ስፔሻላይዝድ ላብራቶሪው የአገሪቱን የውሃ ሃብት ጥራትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ
ነሐሴ 21/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የአገሪቱን የውሃ ሃብት ጥራትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ዘመናዊ የውሃ ጥራት ላብራቶሪ የምረቃ ስነስርዓት ላይ የአገሪቱን የውሃ ሃብት ጥራትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ምዕራፍ ነው ተባለ።
የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በነባሩ ግቢ ውስጥ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጡ ህንፃዎችንና ዘመናዊ የላብራቶሪ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በይፋ ስራ አስጀመረ።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ለአገልግሎት የበቃው ዘርፈብዙ ህንፃ እና ስፔሻላይዝድ ላብራቶሪ ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነትና ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣ የሚያስችል በመሆኑ የጥናት፣ የምርምር እና የልማት ስራዎችንም ያዘምናል ብለዋል።
ስፔሻላይዝድ ላብራቶሪው የአገሪቱን የውሃ ሃብት ጥራትንና ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እንደሀገር ከዘመናዊ ግብርና ወደ ኢንደስትራላይዜሽን ለመሸጋገርም ከፍተኛ እገዛ አለው ነው ያሉት።
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም እንደሀገር የውሃ መጠንና ጥራት ምን ይመስላል የሚለውንም ለመለየት በላብራቶሪ የተደገፈ መሆን ስላለበት ዛሬ እውን ሆኖወደ ስራ እንዲገባ የላቀ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላትም በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታመነ ኃይሉ በበኩላቸው ተቋሙ ለረጅም አመታት በጥናት፣ በምርምርና በስልጠና ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው፤ በይፋ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው ስፔሻላይዝድ ላብራቶሪ ተቋሙ ኃላፊነቱን የበለጠ እንዲወጣም ያግዛል ብለዋል።
ዶ/ር ታመነ አያይዘውም የውሃ ጥራትና ምርምር ላይ በላብራቶሪ አገልግሎት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በተሻለ አቅምና ጥራት ተልዕኳችንን ለመወጣት የሚያስችል አዲስ ምዕራፍ ከመሆኑም በላይ ተቋሙ ለውሃው ዘርፍ ብቁ፣ ተግባራዊ ክህሎት ያለውና ችግር ፈቺ የሆነ የሰው ሀብት ልማት ለማፍራትም ትልቅ አስተዋፅኦ ያደርጋል ነው ያሉት።
በመድረኩ የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አህመድ እና የቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ግቢው የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ፣ ለልምድ ልውውጥ የሚመቹ ቦታዎች፣ ሶስት በአንድ የስፓርት ማዘውተሪያ ሜዳ፣ የመዝናኛና ሌሎች የመሰረተ ልማት ማሻሻያ ቦታዎችን ያካትታል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto