የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎችን የኃይል ጥያቄ የሚመልስ ነው ተባለ
የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎችን የኃይል ጥያቄ የሚመልስ ነው ተባለ
ቁንቢ:- ነሐሴ 09/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በጋራ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ቁንቢ ወረዳ ያስገነባው በሰዓት 850 ኪሎ ዋት የሚየመነጩ የፀሃይ ኃይል ፕሮጀክቶች (Solar Mini-grid) አገልግሎት መስጠት ጀመሩ።
መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎችን የኃይል ጥያቄ የሚመልስ ነው ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ባለፉት አመታት ከግሪድ ርቀው የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኃይል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ጠቁመው፤ በቀጣይ እ.ኤ.አ በ2035 ሰባ ከመቶ ከግሪድ እና ሰላሳ በመቶ ከግሪድ ውጪ የሚኖሩ
የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትን ወክለው የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚው አቶ መላኩ ታዬ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት በተጠናቀቀው በጀት አመት 26 የፀሃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት መብቃታቸውን ጠቁመዋል።
ከአለም ባንክ እና ከኢትዮጵያ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተገነባው በሀሪሮ ከተማ 600 ኪሎ ዋት የሚያመነጨው ፕሮጀክት በ408 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከ2 ሺ 943 አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
በተመሳሳይ በሀሮጉራቲ ቀበሌ 250 ኪሎ ዋት በፀሃይ ኃይል የሚያመነጨው ፕሮጀክት በ232 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከ703 አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው።
በመድረኩ በምስራቅ ሀረርጌ ዞን የቁምቢ ወረዳ አመራሮች፣ የሀሪሮ እና የሀሮ ጉራቲ ከተማ ነዎሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሚመለከታቸው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴ ባለሙያዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto