ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያበለጸጋቸውን የጎርፍና የድርቅ ትንበያ ሞዴሎች አስመገመ።
ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያበለጸጋቸውን የጎርፍና የድርቅ ትንበያ ሞዴሎች አስመገመ።
አዳማ ነሐሴ9/2018ዓም (ው.ኢ.ሚ)
በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ምህረት ደናንቱ እንደገለጹት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የጎርፍ አደጋን ቀድሞ ከመተንበይና ከመከላከል አኳያ ያበለጸጋቸው አብዛኞቹ ሞዴሎች ሥራቸው ያለቀና ለሀገሪቱ የልማት እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው መሆናቸውን ገልጸዋል ።
ፕሮፌሰር ምህረት አክለውም ከዚህ ቀደም ያልነበረንን በሀገር አቀፍ ደረጃ በየትኛው አካባቢና በምን ጊዜ ጎርፍ ሊከሰት እንደሚችል በጊዜ በመተንበይ አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።
በመድረኩ ከተገመገሙት አምስት ሞዴሎች መካከል የከተማ ጎርፍ ትንበያ ሞዴል፣የድርቅ ሁኔታዎችን ቀድሞ የሚተነብይ ሞዴል፣ እና የውሃ ሀብትን ከጎርፍ ጋር በማገናኘት አደጋውን በሰላም ለማሳለፍ የሚያስችሉ ሦስት ሞዴሎች ይገኙበታል ብለዋል ።
በተጨማሪም ፕሮፌሰሩ መረጃን በጥራት ከመሰብሰብና ለተጠቃሚዎች ከማድረስ አኳያ የሚታዩ ክፍተቶችን በሙያዊ እገዛ ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው ትክክለኛና ጥራት ያለው መረጃ በማደራጀት ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የሙያተኞች ዋና ኃላፊነት መሆኑን አሳስበዋል።
በሚኒስቴሩ የሃይድሮሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ታደለ ተስፋዬ በበኩላቸው ባለፉት ዓመታት የተበለጸጉ የሃይድሮሎጂካል ምርቶችን (Hydrological Products) ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም ላይ እንደሚገኙ በመግለጽ ከእነዚህም መካከል የፓይፕ ሞዴል ቨርዥን 2 (PIPE Model Vol. 2): ለጎርፍ ትንበያ የሚያገለግል እንዲሁም የቀጠናው የጋራ ሞዴል (Regional Model): ከዓለም የሜትሮሎጂ ድርጅት (WMO) ጋር በመተባበር ለናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት አገልግሎት የሚሰጥና በሚኒስቴሩ ሰርቨር ላይ የሚጫን ሲሆን ኮንቲኑየም ሞዴል (Continuum Model): በጣሊያን መንግሥት ድጋፍ በአዋሽ፣ በዋቢ ሸበሌና በዳናክል ተፋሰሶች ላይ እየተሞከረ የሚገኝ ገልጸዋል።
እነዚህ ሞዴሎች የጎርፍ ትንበያ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ሶስት ወራትን ያካተተ የድርቅና የውሃ መጠን ሁኔታን የሚያመላክቱ ወቅታዊ መረጃዎችን (Hydrological Bulletins) ለመስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በመጨረሻም፣ የተፈጥሮ አደጋን ሙሉ በሙሉ መከላከል ባይቻልም፣ ቅድመ ማስጠንቀቂያዎችን በመስጠት ግንዛቤው ያለው ህብረተሰብ በመፍጠር የጉዳቱን መጠን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ እንደሚቻል ባለሙያዎቹ አስምረውበታል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto