በኢትዮጵያ የሃይድሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ።

በኢትዮጵያ የሃይድሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ።

​አዳማ ነሀሴ8/2018 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ)

​መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር ሚካኤል መሀሪ እንደገለጹት የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና በተለይም ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለሚከሰቱ ድርቆችና ድንገተኛ የጎርፍ አደጋዎች በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ መሆኗን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ጠንካራና ትክክለኛ የሃይድሮሎጂ ትንበያ መስጠት አሁን ላይ ሳይንሳዊ ቅንጦት ሳይሆን የብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ዶ/ር ሚካኤል በማከል በመርሀ ግብሩ ላይ

​የWHCA ፕሮጀክት እና የብዙ-ሞዴል ስብስብ (Multi-Model Ensemble) የሃይድሮሎጂ ትንበያዎች በአንድ የውሂብ ምንጭ ላይ ብቻ ሳይመሰረቱ የተቀናጁና አስተማማኝ እንዲሆኑ የሚደረጉ ስራዎች ፣​የከተማ ድንገተኛ ጎርፍ ትንበያ (UFFF) በአዲስ አበባ እና እንደ አርባ ምንጭ ባሉ በፍጥነት እያደጉ ባሉ ከተሞች የሰዎችን ህይወትና መሰረተ ልማት ከድንገተኛ ጎርፍ ለመጠበቅ የሚያስችሉ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መሳሪያዎች ማሻሻያ እና​የሞዴሊንግ አቅሞች ማሳደግ ውይይት እንደሚደረግ በመግለጽ በ(ET-HYPE V2 እና Continuum Model) የET-HYPE ሞዴልን ወደ Version 2 ከፍ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፣

​በCIMA Research Foundation የተገነባውንና የጎርፍና ድርቅ ስጋቶችን አስቀድሞ ለመተንበይ የሚረዳውን 'Continuum Model' ተግባራዊ ለማድረግ ለባለሙያዎች ስልጠና እንደሚሠጥም ገልጸዋል ።

በመጨረሻም ​ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በእነዚህ ሞዴሎች የሚዘጋጁ ብሔራዊ የመረጃ ቡለቲኖች እስከ ክልል መንግስታት፣ ለአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኤጀንሲዎች እና ለአርሶ አደር ማህበረሰቦች ዘንድ እንዲደርሱ ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል በማለት ዶ/ር ሚካኤሌ ገልጸዋል ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የገፀ ምድር ውሃ ዴስክ የሆኑት አቶ ሚካኤል ብርሀኔ በበኩላቸው ፕርግራሙ የሃይድሮሎጂ ትንበያና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቶችን የሚያጠናክሩ ሞዴሎችን በማልማት በመተንበይ አደጋን ለመቀነስ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።

​በገጸ-ድር ውሃ ዴስካችን፣ ከኢክፓክ (ICPAC) እና ከዓለም ሜቲዮሮሎጂ ድርጅት (WMO) ጋር በመሆን፣ ትንበያዎቻችን በአንድ ምንጭ ላይ ብቻ የተመሰረቱ ሳይሆኑ ጠንካራና የተቀናጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል ያሉት ኃላፊው በተጨማሪም፣ በእይታ ማቅረቢያ ፕላትፎርሙ (Visualization Platform) ላይ የሚደረገው ማሻሻያ ወሳኝ ነው፤ ምክንያቱም መረጃ ጠቃሚ የሚሆነው እሱን ለመረዳትና ለማስተላለፍ ባለን አቅም ልክ ብቻ ነው ብለዋል።

በመርሀ ግብሩ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዓለም ሜቲዮሮሎጂ ድርጅት (WMO)፣ የኢክፓክ (ICPAC)፣ የኢትዮጵያ ሜቲዮሮሎጂ ኢንስቲትዩት (EMI) ከዩንቨርስቲዎች እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ተመራማሪዎች ተሳትፈዋል።

ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት

ፌስቡክ

https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/

ቴሌግራም

http://t.me/mowieethiopia

ዌብሳይት

http://mowe.gov.et

X/ትዊተር

https://x.com/mowe_ethiopia

ዩቱዩብ

https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s

ቲክቶክ

tiktok.com/@mowetikto

Share this Post