በአውደርእዩ የውሀ ሀብታችን አቅም ያየንበት ነው፡፡

በአውደርእዩ የውሀ ሀብታችን አቅም ያየንበት ነው፡፡ ጳጉሜ 1/2015ዓም (ው.ኢ.ሚ)የመከላከያ ግንባታ ማምረቻ ድርጅት አመራሮችና ሰራተኞች "የውሃ ሀብታችን ለብልፅግና ችን" በሚል በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን አውደርእይ ጎበኙ፡፡ በጉብኝቱ ላይ ያገኘናቸው የመከላከያ ግንባታ ማምረቻ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዋጋዬ ተፈራ አውደርእዩ ሀገራችን በውሀ ሀብትና ኢነርጂ ላይ ያላትን ሀብት ማየት ችለናል ብለዋል፡፡ በተለይ እነዚህ የውሃ ሀብቶች ምን ምን አይነት ናቸው የሚለውን ጭምር ምላሽ የሰጠ ነው ብለው፤ አንድ ሀገር ሀብቷን ለመጠቀም በመጀመሪያ የሀብቷን አይነትና መጠን ማወቅ እንደሚጠይቅ አውስተው፤ በዚህ አውደርእይ ያየሁት በጣም ጠቃሚና ያለንን ሀብት እንዴት ተጠቅመን ለሀገርና ህብረተሰብ ጥቅም ላይ እናውለው የሚለውን መልስ የሰጠና የሚበረታታ ሆኖ አግኝቸዋለሁ በማለት ገልጸዋል።

Share this Post