500 አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በውሃ የሚሠራ የአነስተኛ ኃይል ማመንጫ በአለታ ወንዶ ወረዳ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

500 አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በውሃ የሚሠራ የአነስተኛ ኃይል ማመንጫ በአለታ ወንዶ ወረዳ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የተመራ ቡድን 500 አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ በውሃ የሚሠራ መካከለኛ የኃይል ማመንጫ ጎብኝተዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ማመንጫው

ከ5ኪሎ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም ያላቸው መካከለኛ ኃይል ማመንጫ እንደሚመደቡ አስታውሰው፤ የአለታ ወንዶ ኃይል ማመንጫ እስከ 35 ኪሎ ዋት የማመንጨት አቅም እንዳለው ገልጸዋል።

ይህ ኃይል ማመንጫ ከዋና መስመር ውጨ የሆነና ከአነስተኛ ወንዝ ተጠልፎ በመብራት፣ ለቴሌቪዥን፣ ኮምፒዩተር እንዲሁም ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት እና 17 የሃይማኖት ተቋማት ኃይል በማቅረብ ህብረተሰብ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጨምሮ ገልጸዋል።

በቀጣይም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ለመገንባት መታቀዱንም ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ተናግረዋል ።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም የኃይል አቅርቦትን ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ብቻ ስለማይሸፈን የግል ባለሀብቱ በሁለቱም የታዳሽ ኢነርጂ ምንጮች ላይ እንዲሰማሩ የኢነርጂ ፖሊስ መከለሱን ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ከበደ ጋኖሌ በበኩላቸው አለታ ወንዶ ወረዳ ሃይድፓወር ፕሮጀክት ከ2002 ዓ/ም ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልፀው፤ ባለፈው ዓመት ባጋጠመው ብልሽት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከጂአይዜድ ጋር በመተባበር እንዲጠገን በማድረግ አገልግሎት እንዲጀምር መደረጉን ገልጸዋል። ኃላፊው በቀጣይ ከፍተኛ የህዝቦችን ፍላጎት ለማሟላት በስምጥ ሻለቆች የአነስተኛ እና የመካከለኛው ወንዞች የኃድሮፓወር ጥናቶች እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

Share this Post