መመሪያዎች፣ መደበኛ የአሰራር ሂደቶች (SOPs) እና ማኑዋሎች ይፋ ሆኑ።

መመሪያዎች፣ መደበኛ የአሰራር ሂደቶች (SOPs) እና ማኑዋሎች ይፋ ሆኑ።

ጥቅምት 20/2019ዓም (ው.ኢ.ሚ) በኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የኢትዮጵያ የውሃ እና ኢነርጂ ሳምንት ላይ፣ በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ በላይነህ ይርዳው ዝርዝር ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበዋል።

​በአቀራረባቸውም የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ውጤታማ የሚሆነው የሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎና ቅንጅት ሲታከልበት መሆኑን አብራርተዋል።

እንዲሁም አሰራሩን የበለጠ ጠንካራ፣ ውጤታማ እና ዘላቂ ለማድረግ ከኢኮኖሚያዊ ብቃት፣ ከማህበራዊ ፍትሃዊነት እና ከአካባቢ ጥበቃ አንጻር የገፀ ምድርና የከርሰ ምድር ውሃን ከምድር አጠቃቀም ጋር አጣጥሞ የሚመራ ሁለገብ አቀራረብ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

​በተጨማሪም ዘርፉን ለማጠናከር በሚደረገው ጥረት የሰው ኃይልን፣ አሰራርን እና ግብዓትን በማደራጀት ረገድ ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የቀረበው ጥናት እንደሚያመለክተው እስከአሁን ከተዘጋጁ ሰነዶች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት መመሪያዎች፣ 26 በመቶ የሚሆኑት ስታንዳርዶች (Standards)፣ 7 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የአተገባበር ማኑዋሎች ናቸው።

​በመጨረሻም እነዚህ የተዘጋጁ የህግና የቴክኒክ ሰነዶች መሬት ላይ ያሉ የውሃ ሀብት አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የተዘጋጁ በመሆናቸው ከተጀመረው የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ጋር በማቀናጀት ለተግባራዊነታቸው ይሰራል ተብሏል።

Share this Post