ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የሻንሺ ግዛት ም/ገዥ Mr Wang Xiao እና ከፍተኛ የመንግስትና የቢዝነስ ልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋገሩ።
ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የሻንሺ ግዛት ም/ገዥ Mr Wang Xiao እና ከፍተኛ የመንግስትና የቢዝነስ ልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋገሩ።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በውይይታቸው ኢትዮጵያና ቻይና የቆየ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀው፤ ኢትዮጵያ የኃይል ማመንጫና ስርጭት፣ በመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተለያዩ ኃይል ማመንጫዎችን በመገንባት የጋራ ግንኙነታችንን አጠናክረን እርስ በእርስ በመደጋገፍ በኢኮኖሚ፣ በሶሻልና በፖለቲካው ዘርፍ ብሎም በአቅም ግንባታው ዘርፍ ግንኙነታችንን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ሀብቶች የታዳሽ ኃይል ትኩረት የሚሻው ጉዳይ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የጂኦተርማል፣ የውሃ ኃይልና የንፋስ ኃይል ማመንጫ አቅም ብሎም አረንጓዴ ሃይድሮጂንና ባዮማስ የመሳሰሉት ታዳሽ ኃይል የሚገኝ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ለመጠቀም የፋይናንስ እና የቴክኒክ አቅም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው፤ የቻይና መንግስት በኢነርጂው ዘርፍ በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የኢነርጂ ፖሊሲው የግሉንም ሆነ የውጪ አልሚውን በሚያሳትፍ መልኩ መከለሱንም አስታውሰው ሁሉንም አልሚዎች የሚጋብዝ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡
የሻንሺ ግዛት ም/ገዥ Mr Wang Xiao በበኩላቸው ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በኢነርጂው ዘርፍ ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡