የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከቻይና ህዝብ የፖለቲካ መማክርት ጉባኤ (CPPCC) ሉካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አደረገ።
(ው.ኢ.ሚ) መስከረም/16/2018 ዓ.ም የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሌ የቻይና ህዝብ የፖለቲካ መማክርት ጉባኤ CPPCC የሉካን ቡድን አባላት ጋር በትብብር የመሰራትና መሰል ጉዳዩች ዙሪያ ተወያዩ ፡፡
በውይይቱ ወቅት ክቡር ሚኒስቴር ዲኤታው እንደገለፁት ቻይናና ኢትዮጲያ የሚያመሳስላቸው ሁለቱም ሀገራት ቀደምት የስልጣኔ መፍለቂያ የባህልና የቅርስ ባለቤት መሆናቸው እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
ቻይና ለኢትዮጲያ ሪፎርሙን በመደገፍ በተለያየ ዘርፍ ላይ ድጋፍና ትብብር እያደረገች መሆኑን ገልፅው በኢነርጂ ዘርፍም ለሚደረገው ትብብርና ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅረበዋል፡፡ አክለውም ኢትየጲያ ምንም እንኳን ከሪፎርሙ በኃላ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም የንፁህ መጠጥ ውሀና የኤሌትሪክ ተደራሽ ያልሆነባቸው በርካታ ቦታዎች ከመኖራቸው ጋር ተያይዞ የፋይናሻልና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚስፈልግና ይህንንም ድጋፍና ትብብር እንዲደርጉ ለሉካን ቡድኑ አሳስበዋል፡፡ እንዲሁም ኢትዮጲያ ለግሉ ዘርፍ ምቹ ስነምህዳር በመፍጠር ረገድ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆናለች ያሉት ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው በኢነርጂ ዘርፍም ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታዎች እንደተፈጠረ አሳስበዋል፡፡
የCPPCC ብሔራዊ ኮሚቴ በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮፖዛሎች ምክትል ሊቀመንበር H.ECUI Shaopeng ወደ ኢትዮጲያ ምድር መምጣታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፅው ልኡካን ቡድኑ የመጣበትን ዓላማ በዝርዝር አስረድተዋል። አያይዘውም ቻይና ካላት ህዝብ ቁጥር አኳያ በቂ ውሀ ያላት ሀገር አይደለችም ነገር ግን ያላትን ውሀ በአግባቡ በመጠቀም እና ስነምህዳሩን በመጠበቅ ረገድ በስፋት መሰራቱ ውጤታማና ተሞክሮ የሚወሰድባት ሀገር መሆን ችላለች በማለት ሀሳባቸውን ከገለፁ በኃላ ኢትዮጲያም ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም እንድትችል ስነምህዳርን የመጠበቅ ስራዎች አጠናክራ ልትሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻ ክቡር ሚኒስቴር ዴኤታው ሉካን ቡድኑ የገለፀውን ሀሳብ ትክክል ስለመሆኑ አፅንኦት ሰተው ነገር ግን ኢትዮጲያ ስነምህዳርን በመጠበቅ ደረጃ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሚሆን ሥራዎች እየሰራች መሆኑን አስረድተዋል ፡፡ ለዚህም እንደ አብነት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢኒሼቲፍ እየተሰራ ያለውን የአረጓዴ አሻራና ግሪን ሀይድሮጂን ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው ብለዋል ፡፡ ሉካን ቡድኑም በውሀና ኢነርጂ ዘርፍ ለሚሰሩ ስራዎች ድጋፍና ትብብር እንደሚደርጉ ተናግረዋል ፡፡
በውይይቱ በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ፤ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች ስራ አስፈፃሚዎች የፕሮጀክት አስተባባሪዎች ተገኝተዋል፡፡