በኢትዮጵያ የብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም 3.0 ይፋ ሆነ

በኢትዮጵያ የብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም 3.0 ይፋ ሆነ

ጥቅምት 17/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተዘጋጀው የውሃና ኢነርጂ ሳምንት ሁለተኛው ቀን ላይ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም 3.0 (NEP-3) ይፋ ሆነ።

ኢትዮጵያ ለሁሉም ዜጎች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ፣ የኃይል ደህንነቷን ለማጠናከርና ኤሌክትሪክን ለአገራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ መሠረት ለማድረግ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም 3.0 (National Electrification Program 3.0 — NEP 3.0) ይፋ ሆኗል።

ፕሮግራሙ በሶስተኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት አካል በሆነው የኃይል ዘርፍ ውይይት ውስጥ በጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሚካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ቀርቧል።

የNEP-3 ፕሮግራም ለሁሉም ዜጎች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ አስተማማኝ፣ በተመጣጣኝና ዘላቂ የኤሌክትሪክ አቅርቦትን በማረጋገጥ ለኢኮኖሚያዊ ምርታማነት፣ ለህዝብ አገልግሎቶች፣ ለኃይል ደህንነትና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም ለሚችል ዘላቂ ልማት መሠረት የሚጥል ነው።

ተሳታፊዎቹ የፕሮግራሙን ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ፣ የትግበራ ማዕቀፍ፣ የኤሌክትሪክ አውታር መረብ አፈፃፀም፣ የአቅርቦት ዋጋ ተመጣጣኝነት፣ የፋይናንስ ዘላቂነትና የኢንቨስትመንት ማሰባሰብ ላይ ይወያያሉ።

የNEP 3.0 በፕሮግራሙ ትግበራ ዙሪያ የጋራ መግባባትን ለመፍጠር፣ የተቋማትን ቅንጅት ለማጠናከርና ለተግባራዊ ስኬቱ የሚያስፈልጉ ሀብቶችንና ኢንቨስትመንቶችን ለማሰባሰብ የሚያግዝ ነው።

የኤሌክትሪክ ተደራሽነት የመጨረሻ ግብ ሳይሆን አገራዊ ልማትን ለማጠናከር ብሎም ለምርታማነትና ለህዝብ ተጠቃሚነት መሠረት እንዲሆን ማድረግ የፕሮግራሙ ትኩረት ነው።

በውይይቱ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችንና ሠራተኞችን ጨምሮ የመንግስት ተቋማት፣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ የቁጥጥር አካላት፣ የልማት አጋሮች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ ተወካዮችና ሌሎች ቁልፍ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው።

Share this Post