ከ299 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የሲቪል ስራና የኤሌክትሮመካኒካል መስመር ዝርጋታ የውል ስምምነት ተፈረመ።

ከ299 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የሲቪል ስራና የኤሌክትሮመካኒካል መስመር ዝርጋታ የውል ስምምነት ተፈረመ።   ህዳር 20/2018 ዓ.ም (ውኢሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዋዳ ኢንጂነሪንግ /WADA engineering/ እና በሽርክና ከኤፍኢ/FE construction /ጋር ለኢዋያ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀከት ከ299 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሲቪል ስራና የኤሌክትሮመካኒካል መስመር ዝርጋታ የውል ስምምነት ተፈርሟል።   በውል ስምምነቱ ላይ ተገኝተው የፈረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ የኢዋያ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በቦረና አካባቢ እንደሚገኝ ገልፀው አካባቢው በከፍተኛ ሁኔታ ውሃ አጠርና ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በድርቅ የተጠቃ አካባቢ በመሆኑ ስራው ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ በፍጥነትና በጥራት መሠራት አለበት ብለዋል።   ክቡር ሚኒስትር ድኤታው አክለው የፕሮጀክቱ የዲዛይንና የቁፋሮ ስራ የአካባቢውን የውሃ ችግር ከግንዛቤ በማስገባት በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት የተሰራ በመሆኑ ውሉን የተረከበው ድርጅ በሲቪል ስራና የኤሌክትሮመካኒካል መስመር ዝርጋታው ከበፊቱ የተሻለ አፈጻጸም ማሳየት አለበት ብለዋል።   የዝርጋታ ስራዎቹ 12 ወራትን እንደሚፈጅና የገንዘቡ ምንጭ የዓለም ባንክ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር አስፋው ለስራው ጥራትና ፍጥነት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና የዘርፉ ባለሙያዎች የአቅማቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ብለዋል።   የዋዳ ኢንጂነሪንግ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ አበበ አንበሳ በበኩላቸው ጨረታውን አሸንፈው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር የልማት ስራ ለመስራት ዕድል በማግኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ስራውን በታቀደው ከጊዜና በጀት በጥራትና በፍጥነት ሰርተው እንደሚያስረክቡ ተናግረዋል።

Share this Post