በጎፋ ዞን የከርሰ ምድር ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ ከ169.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የግንባታ ውል ተፈረመ።

በጎፋ ዞን የከርሰ ምድር ውሃ ተደራሽነትን ለማሳደግ ከ169.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የግንባታ ውል ተፈረመ።

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 1/2019ዓ.ም

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ኡባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ቤቶና በአካባቢው ቀበሌዎች የሚከናወነውን የከርሰ ምድር ውሃ ልማት ፕሮጀክት ለማስፈጸም ከሾደብ ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. እና ከኬዲኤች ኢንጂነሪንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. ጋር በ169,422,250.08 ብር የግንባታ ውል ፈርሟል።

ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት ፕሮግራም (Horn of Africa Groundwater for Resilience Program) ማዕቀፍ የሚተገበር ሲሆን፣ በአካባቢው ያለውን የከርሰ ምድር ውሃ ሀብት በማልማት ለማህበረሰቡ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማሻሻልና ዘላቂ የውሃ አቅርቦትን ለማጠናከር ያለመ ነው።

በውሉ መሠረት ፕሮጀክቱ በስምንት ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ ተቋራጮቹ ሥራውን በውሉ ዝርዝር ድንጋጌዎችና በተቀመጡት የጥራት መስፈርቶች መሠረት የማከናወን፣ በአፈጻጸሙ ሂደት የሚከሰቱ ጉድለቶችንም የማረም ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

ሚኒስቴሩም በውሉ መሠረት ለሚከናወነው ሥራ ክፍያ የመፈጸም ኃላፊነት ወስዷል።

በተጨማሪም የፕሮጀክቱ አፈጻጸም የአካባቢና የማህበራዊ ጉዳዮችን በአግባቡ በሚያስተዳድሩ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች መሠረት እንዲከናወን፣ እንዲሁም የተቋራጮቹ ሠራተኞች የሚመሩበት የሥነ ምግባር ደንብ እንዲኖር በውሉ ሰነድ ተካቷል።

ውሉን በሚኒስቴሩ በኩል የፈረሙት የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ኢንጂነር አክሊሉ አዳኝ ናቸው።

Share this Post