ከ156 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ44 ከተሞች የውሃ አገልግሎት ጽ/ ቤቶች የቁሳቁስ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ተደረገ።

ከ156 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ44 ከተሞች የውሃ አገልግሎት ጽ/ ቤቶች የቁሳቁስ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ተደረገ። ህዳር 19/2018 ዓ.ም ውኢሚ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከጣሊያን የልማት ኮርፖሬሽን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ156 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለ44 ከተሞች የውሃ አገልግሎት ጽ/ቤቶች የቁሳቁስ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ተደርጓል።   በርክክብ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ዕቃውን ያስረከቡት እና ንግግር ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ የቁሳቁስ ድጋፉ የተደረገው በ7 ክልሎች በ44 ከተሞች የውሃ አገልግሎት ጽ/ቤቶችን አቅም ለማጎልበት፣ አገልግሎቱን ለማዘመንና ለማሳለጥ እንደሚየግዝ ታስቦ ነው ብለዋል።   ክቡር ሚኒስትር ድኤታ አክለው በ44ቱ ከተሞች ከሚገነቡ የመጠጥ የውሃ ፕሮጀክቶች ከ2ቱ በቀር አብዛኞቹ ተመርቀው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙና የመተሃራንና የጂንካን ጨምሮ ቀሪዎቹ በመጠናቀቅ ላይ ያሉ መሆናቸውን ገልፀው በቅርብ ቀን ተመርቀው አገልግሎ ይሰጣሉ ብለዋል ።   የፕሮጀክቱ አንዱ አካል የሆነው የሰው ሀይልን በዕውቀትና በክህሎት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆንና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመላመድ ውጤታማና ዘመኑን የዋጀ ስራ እንዲሰራ ማገዝ ነው የሉት ክቡር ዶ/ር አምባሳደር በቴክኖሎጂ አጠቃቀምና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለዘርፉ ባለሙያወች ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።   ድጋፍ የተደረገው ዕቃ ባለ2 እግር ሞተር ብስክሌት፣ጄነሬተሮችና ማሽኖች ፣ በርከታ እጅግ ውድና ዘመናዊ ዕቃ በመሆኑ በብዙ ጥንቃቄ በመጠቀም ለታለመለት አላማ ብቻ በማዋል አገልግሎቱን በማሳለጥና በማዘመን፣ ታሪፍ በማሻሻል፣ ገቢን በማሳደግ፣ብድርን በመመለስና ህብረተሰብን በማርካት ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ለተረካቢዎች ክቡር ሚኒስትር ድኤታው አሳስበዋል።   በጣሊያን የልማት ኮርፖሬሽን የዋሽ ፣የአካባቢና የኢነርጂ ኤክስፐርት የሆት ሲልቪያ ቫንዜቶ/SILVIA VANZETTO/Expertwash,environment ,energy/ በበኩላቸው አብረን ለልማት ለመቆም እድል ስላገኘን ደስ ብሎናልና እንኳን ደስ አላችሁ ብለው ዕቃው እጅግ ውድና ዘመናዊ በመሆኑ በጥንቃቄና በሀላፊነት ስሜት በመጠቀም ውጤት ቢታይበት ደስ ይለኛል ብለዋል።  

Share this Post