በ15 ሚሊዮን ብር የተቀናጀ የመረጃ ሲስተም ለማልማት ሶፍትዌር ከሚያለማ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ።

በ15 ሚሊዮን ብር የተቀናጀ የመረጃ ሲስተም ለማልማት ሶፍትዌር ከሚያለማ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈረመ። ህዳር 19/2018 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ15 ሚሊዮን ብር የተቀናጀ የመረጃ ሲስተም ለማልማትና ስራ ላይ ለማዋል ኦክስካ አይቲ ሶሉሽን /OXKA It solution / ከሚባል ሶፍትዌር ከሚያለማ ድርጅት ጋር የውል ስምምነት ተፈራርሟል።   የውል ስምምነቱን የፈረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ የውሃልማት ፈንድ ብድር አስተዳደር በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ደረጃውን በጠበቀ የመረጃ አያያዝ በአይቲ /Information Technology/ መደገፍና ሲስተሙ መዘርጋት ስላለበት የውልስምምነቱ አስፈልጓል ብለዋል።   ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ከዚህ ቀደም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በፋይናንስ ስራ ክፍል በአይቲ ሲስተም ዝርጋታ ጥሩ አፈፃፀም እንደነበረው አውስተው አሁን በውል የተረከቡትን ስራ በተሻለ ጥራት፣ብቃትና ፍጥነት ሰርተው እንዲያስረክቡ አሳስበዋል።   የሲስተሙ መዘርጋት እጅግ አስፈላጊ እና አንገብጋቢ መሆኑን የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ድኤታው ለስራው ጥራትና ፍጥነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚያስፈልገው ሁሉ ከጎናችሁ ለመሆን ዝግጁ ነው ብለዋል። ሶፍትዌር የማልማት ስራው 6 ወራትን እንደሚፈጅና የገንዘቡ ምንጭ ከጣሊያን የልማት ድርጅት ድጋፍ እንደተደረገ ክቡር ዶ/ር አምባሳደር አስፋው ገልፀው ለጣሊያን መንግስት እያሳዩ ላለው የልማት ትብብርና መልካም ወዳጅነት ከፍ ያለ ምስጋና ቀርበዋል።   የኦክስካ አይቲ ሶሉሽን ፒልሲ ማኔጀር /XOKA It solution PLC manager /አቶ ኤልያስ አለማየሁ ድርጅታቸው ከ10 ዓመታት በላይ ሶፍትዌሮችን የማልማት ልምድ እንደነበረው ገልጸው አሁን በውል የወሰደውን ስራ ሀገርን በማልማት ስሜት፣ በተሻለ ጥራትና ፍጥነት ሰርተው ለማስረከብ ቃል እንገባለን ብለዋል።

Share this Post