የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ115 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የማማከር ውል ስምምነት ፈጸመ።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከ115 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የከተሞች ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል የማማከር ውል ስምምነት ከMS አማካሪ ድርጅት ጋር ፈጽሟል።
ጥር 07/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ስምምነቱን የተፈራረሙት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አንዱ የሆነው የሳኒቴሽን መሠረተ ልማት ግንባታ በከተሞች አካባቢ የተሳለጠ አገልግሎት በሚሰጡበት ደረጃ ለማድረስ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ስራው በሁለት ሎት በሰባት ከተሞች ማለትም በሎት አንድ አምቦ፣ወልቂጤ እና ሰበታ ሲሆኑ በሎት ሁለት ባቱ፣አርሲ ነገሌ፣ሮቤ እና ዲላ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
ባጠቃላይ የማማከር እና የዲዛይን ስራው 115ነጥብ 2ሚሊየን ብር በመንግስት በጀት እንደሚተገበር በመግለጽ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት በሚፈለገው የጥራት ደረጃና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ባጠረ ጊዜ ስራውን እንዲያጠናቅቁ አምባሳደር አስፋው አሳስበዋል።
የማማከር ስራውን ውል የወሰዱት የMS አማካሪ ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ደሳለኝ ጌታቸው ለተሰጣቸው እድል አመስግነው ከዚህ በፊት ከሚኒስትሪው ጋር ብዙ ስራዎችን መስራታቸውን አውስተው አሁንም የወሰዱትን ስራ ከተያዘው የጊዜ ገደብ ባጠረ በጥራት ሰርተው እንደሚያስረክቡ በመግለጽ መስሪያ ቤቱም ሆነ ከተሞች መረጃዎችን በመስጠት ትብብር እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።
የማማከር ውል ስምምነቱ በ15ወር የሚጠናቀቅ ነው።