የሌማት ቱሩፋት የሠራተኞችን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ ተመራጭ መፍትሔ እየሆነ ነው

የሌማት ቱሩፋት የሠራተኞችን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ ተመራጭ መፍትሔ እየሆነ ነው

በ250 ዶሮዎች የተጀመረው የላይኛው ቤዚን አስተዳደር ፅህፈት ቤት የዶሮ እርባታ ስራ ለሠራተኞች ተጨባጭ ጥቅም እያስገኘ ነው።

ህዳር 6/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የላይኛው ቤዚን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሠራተኞች በራሳቸው ተነሳሽነትና በጋራ ትብብር የጀመሩት የሌማት ቱሩፋት ተግባር ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገለፁ።

ሠራተኞቹ በጋራ ገንዘብ በማዋጣት 250 ዶሮዎችን በመግዛት በፅ/ቤቱ ግቢ ውስጥ የዶሮ እርባታ ስራ መጀመራቸውን ጠቁመዋል።

በዚህም ከዶሮዎቹ የሚገኘውን እንቁላል ለሠራተኞች በቅናሽ ዋጋ በማቅረብ የኑሮ ውድነቱ በሰራተኛው ላይ የሚያሳድረውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

የዶሮ እርባታ ስራውን የበለጠ በማስፋፋትና ከሚገኘው ገቢ በመጠቀም ተጨማሪ የእንቁላልና የስጋ ዶሮዎችን በማስገባት የሰራተኞችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ዕቅድ መያዛቸውንም ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ወደፊት የወተት ከብቶችን በማርባት ሰራተኞች ከወተትና ከወተት ተዋፅኦ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ዕቅድ እንዳላቸውም አመልክተዋል።

ለዚህ ተግባር ውጤታማነት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እያደረገ ያለውን የሙያዊ ምክርና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድነቅ ሰራተኞቹ ለሚኒስቴ ም/ቤቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የላይኛው ቤዚን አስተዳደር ፅ/ቤት የሰራተኞች ተነሳሽነትና የጋራ ትብብር ውጤት የሆነው ይህ ተግባር የሌማት ቱሩፋት ኢኒሼቲቭ የሰራተኞችን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ፣ የምግብ አቅርቦትን ለማሻሻልና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ ያለውን ፋይዳ የሚያሳይ አበረታች ተሞክሮ ነው።

Share this Post