የውሃና ኢነርጂ ዘርፉ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ቀሪ የሰነድ ዝግጅት ሥራዎችን የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ቢሾፍቱ፡ መስከረም 21/2019 ዓ.ም
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሁለተኛው ዙር የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ተቋማት መካከል በመሆን፣ በሪፎርሙ የዝግጅትና የትግበራ ምዕራፎች ሊከናወኑ የታቀዱ ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ እያከናወነ ይገኛል።
በሪፎርሙ የሰነድ ዝግጅት ሥራዎች በተለይ ትኩረት የተሰጣቸው ሲሆን፣ በቢሾፍቱ የሥራ አመራር ማሠልጠኛ ማዕከል እየተዘጋጁ ያሉ የሪፎርም ሰነዶች ወደ ማጠናቀቂያ ደረጃ መድረሳቸው ተገልጿል።
ሰነዶቹም በሪፎርሙ ዓብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጥልቀት እየተገመገሙ ሲመሩ የቆዩ ሲሆን፣ በግምገማው የተለዩ ክፍተቶችን በማረምና የሰነዶቹን ጥራት በማሻሻል የማጠናቀቂያ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
ሪፎርሙ በጠንካራ አመራርና በባለሙያዎች ተሳትፎ ለአንድ ዓመት ያህል በተቀናጀ መልኩ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት የሪፎርም ሰነዶችን ከማዘጋጀት ባለፈ የተቋሙን የሥራ ባህል፣ የአሠራር ሥርዓትና የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራትም ተከናውነዋል።
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የሰነድ ዝግጅቱ የተደረሰበት ደረጃ፣ በግምገማ የተለዩ ጉዳዮች፣ ቀጣይ የሚከናወኑ የማጠናቀቂያ ሥራዎችና የትግበራ ዝግጅቶች በዝርዝር ተገምግመዋል።
በመሆኑም የተዘጋጁት የሪፎርም ሰነዶች የሚኒስቴሩን የአሠራር ሥርዓት ለማዘመን፣ የአገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍናን ለማሳደግ፣ የዲጂታል አሠራርን ለማስፋፋትና የተቋሙን የሥራ አፈጻጸም ለማጠናከር መሠረት እንደሚሆኑ ተገልጿል።
የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የመንግስት የአገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም የአብይ ኮሚቴ ጸሐፊና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ኦልቀባ ባሼ በማጠቃለያ አስተያየታቸው፣ የተዘጋጁት ሰነዶች የአንድ ዓመት በርካታ ጥረትና ሥራን የፈጀ ሂደት ውጤት በመሆናቸው ጥራታቸውን ለማረጋገጥ በጥንቃቄ መገምገምና ማሻሻል እንደሚገባ ገልጸዋል።
በሂደቱ ውስጥ በርካታ የግል ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው ኮሚቴው ያደረገው ጥረት ተጨባጭ ውጤት እንዲያፈራ ሁሉም አካላት በትኩረትና በኃላፊነት መሥራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በተጨማሪም ለግምገማ በቀረቡት ውጤትን መሠረት ያደረገ የስራ ዝርዝርና ውስብስብነት ሰነዶች ላይ የውስጥ ግንኙነትና ፈጠራን የሚመለከቱ ጉዳዮች እያንዳንዱ በሚመጥነው የሥራ መስክና ኃላፊነት በትክክል እንዲካተቱ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የመስክና የቢሮ ሥራዎችም በግልጽ ተለይተው መታየትና በየሥራ ዘርፉ በተገቢው መንገድ መዘጋጀት እንዳለባቸው በመጥቀስ፣ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ጉዳዮችንም አዘጋጅ ኮሚቴው በጥንቃቄ ተመልክቶ እንዲሻሻሉ አቶ ኦልቀባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto