በመካከለኛው አዋሽ ለሚሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ
መስከረም 09/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በመካከለኛው አዋሽ ለሚሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ።
በአቶ ሱራባ ዳኒ የተመራ የአለም ባንክ ልዑካን እና የኢትዮጲያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት ቡድን በ2019 በጀት አመት በመካከለኛው አዋሽ በአሚባራ፣ በሀሩካ እና በዱለቻ ወረዳዎች ላይ ለሚሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄዷል።
የኢት-ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በበጀት ዓመቱ የሚሰሩ የጎርፍ መከላከል ስራዎች በተመለከተ ዋናው የዲዛይን ስራዎች አልቀው ወደ ግንባታ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን እና ከዚህ በፊት በአካባቢው የነበረውን የጎርፍ ችግር መነሻ በማድረግ ለቡድኑ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ተመስገን ከተማ ገለፃ ተደርጓል፡፡
ከአፋር ክልል የዞን እና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የአዋሽ ቤዚን አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ የተገኙ ሲሆን በዚህ ዓመት ሊሰሩ የታሰቡ የጎርፍ መከላከል ስራዎች በተመለከተ ዋናው የዲዛይን ስራዎች አልቀው ወደ ግንባታ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ተመስገን አክለዋል።
የዓለም ባንክ ቡድኑም በመስክ ምለከታው ወቅት ነባሩ የጎርፍ መከላከያ ዳይክ ያለበትን ሁኔታ እና አካባቢያዊና ማህበራዊ ተፅዕኖ በተመለከተ ሀሳብ በማንሳት ውይይት የተደረገ ሲሆን ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ላይ ግብዓቶችን እና ግብረ-መልስት ተሰጥቷል፡፡
የገቢረሱ ዞን አስተዳደር አቶ መሀመድ ሁሴን ጉረታ በበኩላቸው ቡድኑ በቦታው ተገኝቶ በአካባቢው ያለውን የጎርፍ ችግር ለመመልከት በመምጣቱ አመስግነው በአሚባራ፣ በሀሩካ እና በዱለቻ አካባቢ ተደጋጋሚ ጎርፍ እንደሚከሰትም አክለዋል።
የጎርፍ ክስተቱን በዘላቂነት ለመፍታት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀው፤ ለመስራት የታሰበው የመከላከል ስራ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ወደ ትግበራ እንዲገባና ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል፡፡
በወረዳው የሚገኙ ማህበረሰብ ለዓለም ባንክ ቡድኑ ከፍተኛ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን አካባቢውን በመጎብኘታቸውም አመስግነዋል።
ስለተቋማችን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት
ፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/127Jeg3ch6p/
ቴሌግራም
http://t.me/mowieethiopia
ዌብሳይት
http://mowe.gov.et
X/ትዊተር
https://x.com/mowe_ethiopia
ዩቱዩብ
https://youtube.com/@ministryofwaterandenergy-e8842?s
ቲክቶክ
tiktok.com/@mowetikto