በኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ዓለም አቀፍ የግል ሴክተሩ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀረበ፡፡

በኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ዓለም አቀፍ የግል ሴክተሩ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀረበ፡፡ መጋቢት 17 /2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ እያደገ በመጣው የኢነርጂ ልማት ዓለም አቀፍ የግል አልሚዎች ከመንግስት ጎን በመቆም የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ያስተላለፉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ ናቸው፡፡   ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ጥሪ ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በስካይላይት ሆቴል የኢትዮጵያን የማዕድንና የኢነርጂ ዘርፍ አቅም ማሳደግ በሚል አጀንዳና፣ኢትዮጵያ ለንግድ ተዘጋጅታለች በሚል መልዕክት ለከፍተኛ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ ነው፡፡   እንደክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ ኢትዮጵያ ኢነርጂ ለማመንጨትከሃይድሮፖወር፣ከሶላር፣ከነፋስ፣ከጂኦተርማልና ከሌሎች የሃይል አማራጮች በመጠቀም ኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽ ለማድረግ በምታደርገው ጥረት በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ እየቻለች መሆኑን ገልጸው ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች ደግሞ በዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ የሚጠይቅ ተግባር ነው ብለዋል፡፡   አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ መንግስት በሃገሪቱ የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች በኢነርጂ ሴክተሩ ለመደገፍ ተጨማሪ ሃይል መፍጠር፣ወሳኝ የሆኑ የሃይል ማሰራጫዎችና መስመሮችን መዘርጋት፣የሃይል መሰረተ ልማትን ማስፋፋትና አዳዲሶችን ደግሞ ማሻሻል አስገዳጅ ነውም ብለዋል፡፡እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የሃይል ትስስርን በይበልጥ ማጠናከርና ለጎረቤት ሃገራት በዝቅተኛ ዋጋ መላክና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ማገናኘት፣ሱዳንን ከግብጽ ጋር ለማገናኘት በስፋት እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን ይህ ደግሞ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ስለሚፈልግ የግል ሴክተሩን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡   የግል አልሚውን ለመሳብ የሚያስችሉ በርካታ ምቹ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የኢነርጂ ዘርፍ ፖሊሲ መሻሻሉ፣በዘርፉ ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባር ላይ መዋሉ፣የኢንቨስትመንት ፖሊሲ መከለሱ መልካም አጋጣሚዎች በመሆናቸው የግል ሴክተሩ እድሉን በመጠቀም ከውጪ ገብቶ እንዲሰራና ከመንግስት ጎን ሆኖ የኢነርጂ ዘርፉን ማሳደግ እንዳለበት መልዕክት አስተላፈዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የሃገሪቱ የማዕድን ዘርፍ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ተያያዥ ጉዳዮች የተዳሰሰበት ገለጻ በማዕድን ሚኒስቴር አማካኝነት ቀርቧል፡፡   በመድረኩ ላይ የማዕድን በመርሃ ግብሩ ላይ የሃገሪቱ የማዕድን ዘርፍ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ተያያዥ ጉዳዮች የተዳሰሰበት ገለጻ በማዕድን ሚኒስቴር አማካኝነት ቀርቧል፡፡

Share this Post