ፕሮጀክቶችን በዘመናዊ መንገድ ክትትልና ግምገማ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

ፕሮጀክቶችን በዘመናዊ መንገድ ክትትልና ግምገማ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።   አዳማ:-መጋቢት 16/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት በዘመናዊ መንገድ ክትትልና ግምገማ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።   የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ውጤታማ የጎርፍ በመከላከል ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ሲሆን ስራውን በዘመናዊ መንገድ እንዴት ክትትልና ግምገማ ማድረግ እንደሚቻል በአለም ባንክ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።   በአለም ባንክ የሚሰጠው ስልጠና ፕሮጀክቱ የሚተገበርበት ሳይቶች በትራንስፖርትና በሰው ኃይል እጥረት ምክንያት ተደራሽ ለማድረግ ባይቻል እንኳን ጂ.አይ.ኤስንና ሪሞት ሴንሲንግን (GIS and Remote Sensing) በመጠቀም በቦታው ላይ ሆኖ ከነምስል ሞባይል ወይም ኮምፒውተር በመጠቀም መረጃ መሰብሰብ የሚያግዝ የአሰልጣኞች ስልጠና ነው። የመረጃ አያያዝን ከማዘመን ባሻገር ማንኛውም ፕሮጀክት የክትትልና ግምገማ ስራዎችን ያግዛል።   ስልጠናው ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ከውሃና ኢነርጂ፣ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ አደጋ መከላከል ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት፣ ከአዋሽና ከስምጥ ሸለቆ ሀይቆች ቤዚን የሚመለከታቸው ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

Share this Post