የድንበር ተሻጋሪ ውሃን ጉዳይ በሚመለከት የተካሄዱ ጥናቶች ዓላማ፣ግኝት፣ ማጠቃለያና የመፍትሄ ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት ተደረገ፡፡
መጋቢት /2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተዘጋጀው የሱሉልታ ውሃና የውሃ ዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ ላይ የተለያዩ ጥናቶች በዘርፉ ምሁራንና አጥኚዎች ተጠንተው ተሳታፊዎች ተከፋፍለው በተመደቡባቸው ክፍሎች የቀረቡ ሲሆን በአንደኛው ምድብ የድንበር ተሻጋሪ ውሃን ጉዳይ በሚመለከት የተካሄዱ ጥናቶች ዓላማ፣ ግኝት፣ ማጠቃለያና የመፍትሄ ሀሳቦች ዙሪያ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የጥናቶቹ ርዕሰ ጉዳዮችም ድንበር ተሻጋሪ ውሃዎችን በተለይ የናይል ተፋሰስን በትብብር ለመጠቀም የሚያስችሉ አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦችና መፍትሄዎች፣ በቀጠናው ሃገራት መካከል የርስ በርስ መተማመንና ውይይትን መገንባት፣ ለጥቅም መጋራት ትብብር ለመፍጠር የሚያስችሉ አለም አቀፍ ልምዶች፣ የሃገር ውስጥ ውሃን ማብቃት ለቀጣናዊ ትብብር (ከአዋሽ ተፋሰስ መስኖ አስተዳደር ለውሃ ዲፕሎማሲ የሚወሰዱ ትምህርቶች )በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
አጥኚዎቹ በጥናቶቹ እንደጠቆሙት የናይል ተፋሰስን በጋራ ለመጠቀም ፈጠራ መጠቀምና የሚያስገኛቸው ጥቅሞች፣ ውሃን በጋራ በመጠቀም በኩል መልካም ተሞክሮ ያላቸው ሀገራትን ልምድ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑ፣ የሃገር ውስጥ የውሃ አጠቃቀምን ከአዋሽ ተፋሰስ መስኖ ልማት ትምህርት በመውሰድ በድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ላይ ለሚደረገው የውሃ ዲፕሎማሲ ማዋል ተገቢ መሆኑን ተንትነዋል።
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸዉ የቀረቡ ጥናቶችን አድንቀው የሌሎች ሃገራት ተሞክሮ ስንወስድ ከራስ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማገናዘብ አስፈላጊ መሆኑና ቀደም ሲል ከተጠኑ የጥናት ግኝቶች የተለየ ሃሳብ ቢያነሱ የሚሉና ሌሎች መሰረታዊ አስተያየቶችን ለግሰዋል።