ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ከተሰማሩ የአረብ ኤምሬት ካምፓኒ ልዑካን ጋር ምክክር አደረጉ፡፡
ጥር 05/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ልማትና አቅርቦት ከተሰማሩ የዩናይትድ አረብ ኤምሬት ካምፓኒ ልዑካን ቡድን ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ለሉዑካን ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።
በንግግራቸውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተልዕኮውን ለማሳካት በሶስት ዘርፎች ተደራጅቶ በውሃ ሀብት አስተዳደር ፣ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም በኢነርጂ ልማት ዘርፍ በርካታ መሰረታዊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንና የተገኙ ስኬቶችን በዝርዝር ለሉዕካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጲያ በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ምስራቅ አፍሪካን ተሻግሮ እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ከዚያም የሚያልፍ የተሳሰረ የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማስፋት ራዕይ ሰንቃ እየሰራች መሆኑንም አክለው ገልጸዋል።
ሀገራችን ኢትዮጲያ ከለውጡ ማግስት በውሃ እና ኢነርጂ ልማት ዘርፍ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ቢቻልም ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ ከአቅም ክፍተትና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ላይ የነበሩት ፖሊሲዎች የግል ሴክተሩን አሳታፊ ካለመሆናቸው ጋር ተያይዞ ለበለጠ ስኬት ተግዳሮት ሆነው ቆይተዋል ብለዋል።
እነኝህን ችግሮች ለመሻገር ከቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የአቅም ክፍተት መሙላት ላይ ቢሰማሩ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ያሉትን ክፍተቶች በመሙላት የተሻለ አገልግሎት መስጠት ማስቻል፣ ያለንን የውሃ መጠን አውቆ በአግባቡ መጠቀም፣ የውሃ አጠቃቀም ስርዓቱን ዘመናዊ እንዲሆን ማስቻልና መሰል ስራዎችን በመስራት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑንም አብራርተዋል።
ክቡር ሚኒስቴር ዲኤታው ልኡካን ቡድኑ ያቀረቡትን ሀሳብ ተከትሎ ከስራው ባሻገር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የአቅም ግንባታ ፤ የእውቀት ሽግግር ፤ በዘርፉ ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከማቅረብ ባለፈ የማላመድ ስራዎችንም ጭምር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በሀገራችን ሰፊው የማህበረሰብ ክፍል የማገዶ እንጨት ተጠቃሚ በመሆኑ አማራጭ የሚሆኑ ንፁህ የማብሰያ ዘመናዊ ፈጠራዎች ካሉ ተጨማሪ ተደርጎ ቢያዝ የበለጠ እንደ ኢትዮጲያ ብቻ ሳይሆን እንደ አፍሪካም ተፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ሉዑካን ቡድኑም ክቡር ሚኒስቴር ዲኤታው ያስተላለፉትን መልዕክትና ሀሳብ መሰረት በማድረግ የመጡበትን ዓላማ በግልፅ አስረድተዋል።
ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘርፉ ሙያተኞችና ተሳታፊዎች ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች በልኡካን ቡድኑ ምላሽ ተሰቶበታል።