ሰነዶቹ ለትግበራ በሚመችና በሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት በጥራት እየተዘጋጁ መሆኑ ተገለጸ።

ሰነዶቹ ለትግበራ በሚመችና በሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት በጥራት እየተዘጋጁ መሆኑ ተገለጸ። ታህሳስ 15/2018ዓ.ም (ው .ኢ .ሚ) የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የዝግጅት ምዕራፍ ሰነዶች ለዘርፉ የሪፎርም ትግበራ በሚመችና በሀገራዊ የሪፎርም አቅጣጫ መሰረት በጥራት እየተዘጋጁ ነው ተብሏል።   በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን አስመልክቶ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ክፍል በቢሾፍቱ ሰራ አመራር ኢንስቲትዩት ተገኝቶ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚና የውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ሪፎርም የዋናው መስሪያ ቤት ቴክኒካል ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የዝግጅቱ አስተባባሪ የሆኑትን አቶ አለሙ መንገሻን ቃለ መጠይቅ አድርጓል። እንደ ሀገር በሁለተኛው ምድብ ወደ ሪፎርም ከገቡ ተቋማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አንዱ መሆኑን የገለጹት አቶ አለሙ በዝግጅት ምዕራፍ መከናወን ያለባቸውን ሰነዶች ለማዘጋጀት ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ ከተገባ ከሶስት ወር በላይ መሆኑን ገልጸዋል።   የሪፎርም ኮሚቴው ስልጠና ወስዶ በመጀመሪያው ዙር በቢሾፍቱ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት በነበረው ቆይታ ከ15 በላይ ሰነዶች ተዘጋጅቸው ለማንጅመን ቀርበው ከተገመገሙ በኋላ ወደ ሁለቸኛው የሪፎርም ሰነድ ዝግጅት እንደተገባ ገልጸውልናል። ሁለተኛው ዙር የሰነድ ዝግጅት ሂደትም በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ነው ያሉት አቶ አለሙ ሰነዶቹ በቀጣይ በምዘና ሂደት ውስጥ አልፈው የዘርፉን አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ያሳካሉ በሚል እሳቤ እየተዘጋጁ ነው ብለዋል።   ሰነዶቹ ሲጠናቀቁ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የምዘና ሂደት ተደርጎባቸው ወደ ትግበራ ይገባልም ብለዋል። ዘርፉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ስታንደርዳቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት አቶ አለሙ ወደ መሶብ አገልግሎት ቢገቡ የዘርፉን አሰራር ያቀላጥፋሉ የተባሉ አገልግሎቾች ተለይተው በአመራሩ ውሳኔ እንደሚሰጥባቸውም ነው የገለጹልን።   እንደ ሀገር ከ120 ዓመታት በላይ የቆየውን የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት በተሻለና የህዝብን ጥቅም እና ፍላጎት በሚያሟላ መልኩ ለመተግበር መሠረታዊ የሆነ ሪፎርም እየተካሄደ ነው ያሉት አቶ አለሙ ሪፎርሙ ከዚህ ባለው ኮሚቴ ብቻ የሚሳካ ሳይሆን አጠቃላይ የዘርፉን አመራርና ሠራተኛ ድጋፍ እና እገዛ የሚጠይቅ በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።   በዚህም መሠረት አጠቃላይ ለአመራሩ እና ለሰራተኛው በሀገርም ሆነ በተቋም ደረጃ ምን እየተሰራ እንዳለና አጠቃላይ የሪፎርሙን እንድምታ በሚመለከት ኦረንቴሽን እና ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በመጨረሻም ሪፎርሙን ማገዝና ለውጤት ማብቃት የሁላችንም ሀላፊነት እና አደራ መሆኑን አውቀን ለውጤታማነቱ የሚጠበቅብንን ሁሉ መፈጸም ይገባናል ሲሉ አቶ አለሙ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Share this Post