የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ክልል የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታን ከሚሰሩ ውሃቢሮ ፣ አማካሪ ድርጂቶችና ኮንትራክተሮች ጋር ተወያዬ፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በመንግስት በጀት የሚደገፉ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታን ከሚሰሩ ውሃቢሮ ፣ አማካሪ ድርጂቶችና ኮንትራክተሮች ጋር በስራ አፈጻጸምና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
ታህሳስ14/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በአማራ ክልል በመንግስት በጀት በሚደገፉ የCR-WaSH የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ከክልል ውሃቢሮ ፣ አማካሪ ድርጂቶችና ኮንትራክተሮች ጋር ውይይት ያደረጉት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ በክልሉ እየተተገበሩ ያሉ በቅርቡ የሚጠናቀቁና እና አዲስ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው የውይይቱ አላማ ከፕሮጀክቶቹ በዚህ አመት ሊጠናቀቁ የሚችሉ በእቅድ የተያዙ መኖራቸውን ገልጸው በታሰበው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ውሃ ቢሮ፣ ስራ ተቋራጭ እና አማካሪው በጋራ በመሆን ያሉትን ችግሮች በመፍታት ቀሪ ስራዎች እንዲጠናቀቁና የታለመለትን አላማ እንዲያሳኩ ለማድረግም ነው ብለዋል፡፡
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር መጠጥ ውሃ አቅርቦት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታምሩ ገደፋ በበኩላቸው በውይይቱ እያንዳንዱ ፕሮጀክት መታየቱን ገልጸው ፕሮጀክቶቹ አብዛኛው የሚተገበሩት በክልሉ በጣም ድርቅ የሚያጠቃቸውና የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው ዋግህምራ ዞን፣ሰሜን ወሎ፣ደቡብ ወሎና በኦሮሚያ ልዩ ዞን አካባቢዎች የባለ ብዙ መንደር መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ከአንድ መንደር በላይ የሚገናኙ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ናቸው ብለዋል።
አቶ ታምሩ በማያያዝ ለዚህም የዙሀሙሲትን ብንወስድ ኤልክትሮ መካኒክን ሳይጨምር ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይና ሌሎች ትላልቅ ፕሮጀክቶችን የሚጠቃልል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
በክልሉ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ደረጃ ውል የተገቡና ሚኒስትሪው ለክልሉ ውሃ ቢሮ ውክልና በመስጠት በነሱ በኩል ከ10 በላይ ውል የተገቡ ስራተቋራጮች እንዳሉ ገልጸው ከአካባቢው ጸጥታ ጋር በተገናኘ እና ተጨማሪ ችግሮች የዘገዩ ፕሮጀክቶችን ትኩረት ሰጥተን የተመደበላቸው የአመቱን በጀት በመጠቀም ለማህበረሰቡ የታለመውን እቅድ ለማሳካት ጥረት እየተደረገ እንደሆነም አቶ ታምሩ ገልጸዋል፡፡
ባጠቃላይ በክልሉ ያለውን የመጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት እየተሰራና በተለይ በተደጋጋሚ ድርቅ በሚያጠቃቸው አካባቢዎች ዘላቂነት ያለውና ድርቅን መቋቋም የሚችል መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ከ300 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመጠጥ ውሃ ችግር እንዲፈታ ከመድረኩ ተገልጿል፡፡