ለሕዝባችን ሁለንተናዊ የውሃ አቅርቦትና የንፅህና አጠባበቅ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከገንዘብ ድጋፍ በላይ ውጤታማ አፈፃፀም በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ።

ለሕዝባችን ሁለንተናዊ የውሃ አቅርቦትና የንፅህና አጠባበቅ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከገንዘብ ድጋፍ በላይ ውጤታማ አፈፃፀም በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ። የአፍሪካ ቀንድ የከርሰ ምድር መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የመካከለኛ ጊዜ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ለሕዝባችን ሁለንተናዊ የውሃ አቅርቦትና የንፅህና አጠባበቅ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከገንዘብ ድጋፍ በላይ ውጤታማ አፈፃፀም በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ።   ህዳር 23/2018ዓም (ው.ኢ.ሚ) መርሀ ግብሩን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ፒ..ኤች.ዲ) ባለፉት 3 ዓመታት የፕሮጀክቱን የአፈጻጸም ሂደት ለመገምገም እና በቀሪ ሦስት ዓመታት የፕሮጀክቱን ዓላማ ለማሳካት ለሚመጡት 3 ዓመታት የፕሮጀክት ትግበራ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መንግስትን እና ዓለም ባንክን የሚያጣምረው ይህ የግምገማ መድረክ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡   የአውደ ጥናቱ ዋና ዓላማም ባለፉት ሶስት ዓመታት የፕሮጀክቱን የትግበራ ሂደት መገምገም፣ የተገኙትን ተሞክሮዎችና ትምህርቶች፣ ተግዳሮቶችን እና አተገባበሩን ለማሻሻል እና የፕሮጀክቱን ግብ ለማሳካት ስልቶችን ማስቀመጥ ነውም ብለዋል። በዚህ ፕሮጀክት ትግበራ ወቅት የተማሩት እጅግ በጣም ብዙ ትምህርቶች አሉ እና ይህ አውደ ጥናት በክልል ደረጃ ለማስፋት፣ ለማሰራጨት እንዲሁም ተግዳሮቶችን እና ክፍተቶችን ለመፍታት ፣ ለማሻሻል እና ኢንቨስትመንቶችን ቅድሚያ ለመስጠት ምርጥ ትምህርቶችን እና ስኬታማ ልምዶችን በትክክል ለመለየት ይረዳናል በማለት ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።   በፕሮጀክት ትግበራ እና በፋይናንስ አቅርቦት ላይ ጫና ያስከተሉ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ ከ100,000 በላይ ለሆኑ የገጠር ማህበረሰቦች የውሃ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ መቻሉንም ገልጸዋል። ለሕዝባችን ሁለንተናዊ የውሃ አቅርቦትና የንፅህና አጠባበቅ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ፣ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የኢኮኖሚ እድገቱን ለማስቀጠል፣ በቂ የገንዘብ ድጋፍ በስፋት ማግኘት እና ውጤታማ አፈፃፀም እኩል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ይህንን እድል ማግኘት ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ላሳስባችሁ እፈልጋለሁ በማለት ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።   በሚቀጥሉት ቀሪ ሶስት የፕሮጀክቱ ዓመታት ውስጥ ያሉትን ሀብቶች በሚገባ በመጠቀም መተግበር የፕሮጀክቱን ግብ ለማሳካት እና ተጨማሪ ገንዘብ ለማምጣት ወሳኝ ነውም ብለዋል፡፡ በመጨረሻም፣ ለአዘጋጅ ኮሚቴው እና በተለይም ለዓለም ባንክ ተወካዮች ምስጋናቸውን በማቅረብ ለኢኮኖሚ ልማት እና ለቀጠናዊ ትብብር የከርሰ ምድር ውሃችንን በአግባቡ መገምገም፣ ማዳበር እና በዘላቂነት ማስተዳደር እንድንችል አብሮ መስራታችንን እንቀጥል በማለት አሳስበዋል።   በመርሀ ግብሩ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት የሶስት ዓመት ሪፖርት ግኝት የቀረበ ሲሆን በሪፖርቶቹ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገና ለቀረቡት ጥያቄና አስተያየቶችም ከመድረክ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

Share this Post