በምንሰራው ስራ ሁሉንም ተጠቃሚ ሰናደርግ የምናከብረው በዓል ውጤታማና ትርጉም ያለው ይሆናል ሲሉ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገለጹ።

በምንሰራው ስራ ሁሉንም ተጠቃሚ ሰናደርግ የምናከብረው በዓል ውጤታማና ትርጉም ያለው ይሆናል ሲሉ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገለጹ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሰራተኞች 20ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ''ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረብሄራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ።   ህዳር22/2018ዓም(ው.እ.ሚ) በበአሉ ላይ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በምንሰራው ስራ ሁሉንም ተጠቃሚ ሰናደርግ የምናከብረው በዓል ውጤታማና ትርጉም ያለው ይሆናል ብለዋል። ህገ መንግስቱ ከጸደቀበት 1987ዓ.ም ጀምሮ ኢትዮጵያ ህብረብሔራዊ ሀገር መሆኗ የተረጋገጠበት፣ በጋራ ቆመን ብዙ ስኬቶችን ያስመዘገብንበት እንዲሁም ልዩነታችን ውበታችን መሆኑን በተግባር ያሳየንበት የድል በዓላችን መሆኑን ልንረዳ ይገባልም ብለዋል።   በዓሉ ህዝቦች በራሳቸው ቋንቋ ፣ባህል ፣ ማንነት እንዲኮሩና ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተከባብረው እንዲኖሩ ትልቅ አበርክቶ አድርጓል ብለዋል። እንደ ሀገር አብረን ቆመን በርካታ ስኬቶችን አስመዝግበናል ለዚህ ደግሞ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስኬት የብሔር ብሔረሰቦች ድምር ውጤት መሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል ክቡር ሚኒስትሩ።   በህብር መቆም የሚጎዳን ሳይሆን አንድ የሚያደርገን ጉዳይ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ እንደ ተቋምም የምንሰራቸው የውሃ ሀብት አስተዳደር፣ የመጠጥ ውሃና የኢነርጂ ልማቶች ሁሉንም ያሳተፉና ተጠቃሚነትን ያረጋገጡ እንዲሆኑ ከምንጊዜውም በተሻለ ሁኔታ እየሰራን ነው ብለዋል። አሁን ያለንበት የምርጫ ወቅት ፍትሃዊና ሰላማዊ እንዲሆን በጋራ የምንቆምበት በመሆኑ በጋራ ሆነን አንድ ጠንካራ ሀገር መገንባት ላይ እየሰራን ነው ብለዋል።   በአሉን አስመልክቶ የዲሞክራሲያዊ ጽንሰ ሀሳብ እና ባህሪያት፣ ፌዴራላዊ ዲሞ ክራሲ በኢትዮጵያ፣ የኢፌድሪ ህገ መንግስት ና ፌደራላዊ ዲሞክራሲ ዙሪያ የተዘጋጀውን ሰነድ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ስሜ በሰፊው አቅርበዋል። በቀረበው ሰነድ ላይ በሰፊው ውይይት ተደርጎበታል።

Share this Post