የቅድመ ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን አስመልክቶ በውሃና ኢነርጂ ሚ/ር የተዘጋጀው አውደ ርእይ ላይ ለተሳተፉ የልማት አጋሮችና እና የግል ድርጅቶች እውቅና ተሰጠ።
ጥቅምት 7/2018ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና
ኢነርጂ ሚኒስቴር የቅድመ ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን አስመልክቶ ተዘጋጅቶ በነበረው አውደርይ ላይ አስተዋጾ ላበረከቱ የልማት አጋሮችና እና የግል ድርጅቶች እውቅና ተሰጠ።
በመርሀ ግብሩ ተገኝተው እውቅና የሰጡት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ አውደ ርዕዩ በውሃውና በኢነርጂው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚያስችሉ መሆናቸውን ለማሳየት ታስቦ የተዘጋጀ እንደነበር ገልጸዋል።
እንደ ሀገር የታዳሽ ሀይል ልማት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ እያደረገ ያለውን አስተዋጾ ለማሳየት ብሎም በሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠርና የአፍሪካን የአየር ንብረት ለውጥ ለመግታት መፍትሄ እንደሆነች ለማሳየት አላማ እንደነበረውም አክለዋል።
በተጨማሪም በታዳሽ ሀይል ልማት ላይ የተሰማሩት የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ልምድ እንዲወስዱም ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ ዓውደ ርእይ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡
የታዳሽ ሀይል ልማት የማህበረሰቡን ኑሮ ለማሻሻል፣ ለግብርና ልማትና ለውሃ አቅርቦት እያደረገ ያለውን አስተዋጾ መረዳት እንዲቻልም አውደርዕዩ ጥሩ ከበርከቶ ነበረው ብለዋል ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው።
የንጹህ ማብሰያ ቴክኖሎጂና የሀይል ቆጣቢ ምድጃዎችን በስፋት ማስዋወቅ እንደተቻለም ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው አብራርተዋል፡፡
በአውደ ርእዩ ከፍተኛ አስተዋጾ ላደረጉ የልማት አጋሮችና እና የግል ድርጅቶች እውቅና ሰጥቷል፡፡