ለውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ለተጠሪ ተቋማት እና ለፅ/ቤት አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ሱሉልታ፤ መስከረም 26/2018 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ለውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ለተጠሪ ተቋማት እና ለፅ/ቤት አመራሮች በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
ስትራቴጂያዊ አመራር በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሚሰጠው ስልጠና የውሃ ኃይል እና የስልጣኔ መሠረቶች ምን ምን እንደሆኑ፤ በሲቪላይዜሽንና በሞደርናይዜሽንም ዙሪያ የሚያተኩረው ስልጠና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚደንት በክቡር አቶ ዛዲቅ አብርሃ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በስልጠናው ላይ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ስልጠናው ለቀጣይ ስራችን እንደስንቅ የምንጠቀምበትና ለአቅም ግንባታ መሰረት የሆነውን ዲሲፕሊንን የምንገነባበት ነው ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም የስልጣኔያችን ውድቀት መንስኤዎች ምንድን ናቸው፤ ከውድቀቱስ ምን እንማራለን የሚለውንም የምናይበት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ሁሉም ሰልጣኞች አመራር እንደመሆናችሁ በየጊዜው የተሰጡ ስልጠናዎችንም ለማደስና ለማስታወስ ስለሚጠቅም በንቃት እንድትሳተፉ አደራ በማለት ክቡር ሚኒስትሩ አሳስበዋል።
ክቡር አቶ ዛዲግ አብርሃ ስልጠናውን በሚሰጡበት ወቅት ውሃ የተፈጥሮ ሀብት ብቻ ሳይሆን የስልጣኔ መሰረት፣ የስነ-ምህዳር ደም ስር፣ የሞራል እና የባህል እሴቶቻችን መስታወት ነው በማለት የውሃ ኃይል እና የስልጣኔ መሠረቶችን በዝርዝር አብራርተዋል።
በስልጠናው ከ200 በላይ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን ለ5 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ የተያዘው መርሃ ግብር ያመላክታል፡፡